ግልጽ የጨረታ  ማስታወቂያ የግዥ መለያ ቁጥር ግ/ጨ/03/2019

0
50

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ዲስክ ቶኘ ኮምፒተር እና ኘሪተር  ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ብር 500,000 (አምስት መቶ ሽህ) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ. 1 እስከ 3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙ የአገልግሎት ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሰስት መቶ)  ብቻ በመክፈል ከግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 315  ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ማግኘት ወይም መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 315  ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ማግኘት ወይም መግዛት ይቻላል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድቦንድ) ለሚወዳደሩበት የዕቃ ግዥ ብር 20,000 (ሃያ ሽህ ) ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በአብክመ ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ከግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ዳይሬክቶሬት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በ11ኛው ቀን አስከ 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 315 በ11ኛው ቀን 3፡30  ተዘግቶ 4፡00 ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በ3.00 ተዘግቶ 4፡00  ይከፈታል፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 315 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 9644/058 220 9646 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት

ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ

ባህርዳር

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here