የአማራ ክልል ስቴት ዩኒቨርሲቲ ለ2019 በጀት ዓመት ለስልጠና አገልግሎት የሚውል ሎት 1. የወፍጮ አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ማስፈጨት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- ከመንግስት የሚጠበቅባቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በየሎቱ በመክፈል በዩኒቨርሲቲው ግቢ ቢሮ ቁጥር 19 መግዛት ይችላሉ፡፡
- የሚገዙ የዕቃዎችን አገልግሎቶችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በመግለጽ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ከጥቅምት 09/2019 ዓ/ም ጀምሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በዩኒቨርሲቲው የግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 19 ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ሎት በጨረታ ሰነዱ የተገለፀውን የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን አንድ ወጥ በሆነ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ በዩኒቨርሲቲው ግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ወይም ቢሮ ቁጥር 19 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጥቅምት 09/2019 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 18/2019 ዓ.ም 9፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ጥቅምት 18/2019 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዩኒቨርሲቲው አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- የመክፈቻው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ዩኒቨርስቲው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለዉም፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 19 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 23 60 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአማራ ክልል ስቴት ዩኒቨርሲቲ

