የጎንደር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን በመ/ቤቱ ላሉ የሥራ ሂደቶች ለአዘዞና ለጠዳ ንዑስ ወረዳ ፍ/ቤቶች አገልግሎት የሚሰጡ የተለያዩ እቃዎችና አገልግሎቶችን በግልጽ ጨረታ ግዥ ለመፈፀም ሎት 01. የደንብ ልብስ፣ ሎት 02. ከጥጥ የተሰራ ካፖርት ሸሚዝ የዝናብ ልብስና ጥላ፣ ሎት 03. የአገር ውስጥ የሴትና የወንድ አጭር ቆዳ ጫማና ፕላስቲክ ቦት ጫማ፣ ሎት 4. የጽህፈት መሳሪያዎች አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ሎት 05. የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 06. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 07. የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎች፣ ሎት 08. የህትመት ውጤቶችና ቲተሮች እና ሎት 09. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና የእጅ ዋጋ ግዥዎችን መፈጸም ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች በየሎቱ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ያሳደሱ በዘመኑ ግብር የከፈሉ እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት አያይዘው ከጨረታ ሰነዱ ጋር የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው፡፡ ከብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ለሚያቀርቡ ጠቅላላ ዋጋ ድምርና ለኤሌክትሮኒክስ ነክ እቃዎች ለሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡ የጨረታ ሰነዱ የሚሸጥበት የማይመለስ ከሎት እስከ ሎት 3. እና ሎት 9. ብር 200 (ሁለት መቶ ብር)፣ ከሎት 4 እስከ ሎት 8. ብር 400 (አራት መቶ) ብር በመክፈል ከጎ/ከ/ወ/ፍ/ቤት የግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ማስታወቂያው ከጥቅምት 09/2019 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 18/2018 ዓ/ም ጨረታው ቆይቶ ጥቅምት 19/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በታሸገበት ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በጎ/ከ/ወ/ፍ/ቤት ግዥ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 በግልጽ ይከፈታል፡፡
- የሚገዙ እቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ወይም (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በተናጥል (በየሎት) ከሞሉት ዋጋ ለእያንዳንዱ ሎት አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ከመ/ቤታችን ግዥ ፋይናንስ/ን/አስ/ድን ቢሮ ቁጥር 05 ከገንዘብ ያዥ በመሂ 1 ለማስያዙ የግቢ ደረሰኝ አስቆርጦ ከሚወዳደርበት ሰነድ ጋር አብሮ ፎቶ ኮፒውን በማሸግ ማስያዝ ያለባቸው ሲሆን የጨረታ ማስከበሪያውን በየሎቱ በተናጠል በመለየት ማስገባት አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ 2 ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ (ኮፒ) በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ጎ/ከ/ወ/ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 እስከ ጥቅምት 19/2019 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 3፡00 ድረስ ሰነዱን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ የእቃውን መጓጓዣና እንዲሁም ማናቸውም የመንግስት ታክስ ያካተተ ሆኖ መቅረብ አለበት፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በቀኑና በሰዓቱ ካልተገኙ ጨረታውን ከመክፈት አያግድም፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ውድድሩ በሎት ድምር ወይም በነጠላ ዋጋ የማወዳደር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃ ጎ/ከ/ወ/ፍ/ቤት ድረስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የሚጠገን የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን የእጅ ዋጋ ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡ የሚጠገኑ እቃዎች የሚጠገኑበት ቦታ ጎንደር ከተማ ወ/ፍ/ቤት በመ/ቤቱ ላሉ የሥራ ሂደቶችና፣ ለአዘዞና ለጠዳ ንዑስ ወረዳ ፍ/ቤቶች ይሆናል፡፡
- ሁሉንም እቃዎች ናሙና ከመ/ቤቱ ማየት ይችላሉ፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በጎንደር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 126 00 36 መደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የጎንደር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት

