ለ2ኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

0
25

የጸደይ ባንክ አ.ማ ለምቾት ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለሰጠው ብድር በመያዣ የያዛቸውንና ዝርዝር ሁኔታቸው ከዚህ በታች የተገለጹትን ንብረቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ የተበዳሪ ስም የንብረት አስያዥ ስም የንብረቱ መገኛ እና ካርታ ቁጥር መነሻ ግምት
 

1

 

ምቾት ኃ/የተ/የግ/ማህበር

 

አቶ ታፈረ ወርቁ መራ

በአብክመ በቡሬ ከተማ ቀበሌ 03 የሚገኝ ካርታ ቁጥር 16421/2013  

2‚487‚661.37

 

2

 

ምቾት ኃ/የተ/የግ/ማህበር

 

አቶ ታፈረ ወርቁ መራ

በአብክመ በቡሬ ከተማ ቀበሌ 02 የሚገኝ ካርታ ቁጥር 16422/2013  

1‚831‚779.94

 

3

 

 

ምቾት ኃ/የተ/የግ/ማህበር

 

አቶ ታፈረ ወርቁ መራ

በአብክመ በቡሬ ከተማ ቀበሌ 02 የሚገኝ ካርታ ቁጥር 9005/2008  

2‚119‚342.42

 

በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ደንቦችና ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት የሚችሉ ተጫራቾች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል፡፡

  1. ተጫራቾች የቤቱን የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ኛውን (በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ) በፀደይ ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት ለጨረታ መስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. በጨረታው የሚሳተፉ በሕግ ሰውነት ያገኙ ከሆነ የድርጅቱን መመስረቻ ጽሑፍ ወይም መተዳደሪያ ደንብ ፤ሕጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ሕጋዊ ውክልና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ የሚረጋገጠው የጨረታው ውጤት በሚመለከተው አካል ጸድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠው ይሆናል፡፡
  4. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈልና በጨረታ ያሸነፈውን ንብረት መረከብ ይኖርበታል፡፡ አሸናፊው በ15 ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ያሆናል፡፡
  5. በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ይመለስላቸዋል፡፡
  6. የጨረታ አሸናፊው ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች ፣ግብር፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ 15 በመቶ የሚከፈል ከሆነ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማንኛውንም ወጭዎች ይሸፍናል፡፡ ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሆኖ ለቀሪው የሊዝ ክፍያ ገዠው ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ውል ይይዛል፡፡
  7. ተጫራቾች ቤቱን በባንኩ አማካኝነት መጎበኘት ወይም ማየት ይችላሉ፡፡
  8. ጨረታው ግንቦት 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ፍኖተ ሰላም ከተማ ከሚገኘው የፀደይ ባንክ ፍኖተ ሰላም ዲስትሪክት ቢሮ ግራውንድ ይካሄዳል፡፡
  9. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 18 56 02 75 መደወል ይቻላል፡፡

የጸደይ ባንክ አ.ማ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here