ፀደይ ባንክ (አ.ማ) እንጅባራ ቅርንጫፍ ለአቶ ጌትነት መንግስት እና ወ/ሮ ገነት ባይነሰኝ እንዲሁም ለአቶ ሃይለማርያም አላምረው እና ወ/ሮ እመቤት አማረ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውን በሰንጠረዥ ከዚህ በታች የተገለፁ መያዣዎችን ለመጀመሪያ ጊዜ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና በተሸሻለው አዋጅ ቁጥር 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የቤቱን የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ ኛውን (በጥሬ ገንዘብ ወይም ሲፒኦ በፀደይ ባንክ አ/ማ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ መያዝ ይገባቸዋል፡፡ በጨረታው የሚሳተፈው በሕግ ሰውነት ያገኘ ሰው ከሆነ የፀደቀ የድርጅቱ መመሥረቻ ጽሑፍ ወይም መተዳደሪያ ደንብ፣ ሕጋዊ ሰውነት ያገኘበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ ቃለ ጉባኤ ወይም ሕጋዊ የውክልና ሠነድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ አሸናፊው አሸናፊነቱ የሚረጋገጠው የጨረታው ውጤት በሚመለከተው አካል ጸድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠው ይሆናል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 ቀን ውስጥ አጠቃልሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሜ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡ ላላሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ይመለስላቸዋል፡፡
- የጨረታ አሸናፊው ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግሥት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ 15 በመቶ ተጨማሪ እሴት ታክስ የሚከፈል ከሆነ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጭዎች ይከፍላሉ፡፡
- ተጫራቾች ቤቱን በባንኩ አማካኝነት ጨረታው ከመካሄዱ በፊት አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ወይም ማየት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው ቦታ በእንጅባራ ከተማ፣ 01 ቀበሌ በሚገኘው የፀደይ ባንክ አ.ማ እንጅባራ ዲስትሪከት 3ኛ ፎቅ በሚገኘው አዳራሽ ውስጥ ነው፡፡
- ባንኩ ለሽያጭ ያቀረበውን ንብረት የሚሸጠው በጥሬ ገንዘብ ወይም በከፊል ብድር ሲሆን አሸናፊው በባንኩ የብድር ፖሊሲ መሰረት አስፈላጊውን መስፈርቶች ካሟላ ንብረቱን በከፊል ብድር ለመግዛት መጠየቅ ይችላል፡፡
- የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት 30 ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል፡፡
- ከፍተኛ ዋጋ የሰጠው ተጫራች የጨረታው አሸናፊ ነው የሚባለው ከባንኩ አሸናፊነቱን የሚገልጽ ደብደቤ በፁኁፍ ሲደርሰው ብቻ ነው፡፡
- ንብረቱ በገዥው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብደቤ ይጽፈል፡፡
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 058 227 07 08 እና 09 10 30 20 03 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
| የተበዳሪው ስም | የመያዣ ሰጪ ስም | የካርታ ቁጥር/የይዞታውመላያ ቁጥር | ቤቱ የሚገኝ በት ቦታ | የቦታው ስፋት በካ/ሜ | የንብረቱ አይነትና አገልግሎት | የጨረታ መነሻ ዋጋ | የጨረታ ቀንና ሰአት | ጨረታ የወጣው | ||
| ጌትነት መንግስት እና ገነት ባይነሰኝ | ጌትነት መንግስት እና ገነት ባይነሰኝ
|
1190/13 | አዘና ከተማ 01 ቀበሌ | 500 ካ/ሜ | ድርጅት | 5,688,880.73 | 20/09/2018 ዓ/ም ከ4፡00-6፡00 | ለመጃመሪያ ጊዜ | ||
| ሀ/ማርያም አላምራው እና እመቤት አማረ
|
ሀ/ማርያም አላምራው እና እመቤት አማረ
|
AM010011520007 |
እንጅባራ ከተማ |
517.13 ካ.ሜ |
ለእንጨትና ብረታብረት |
6,026,077.71 | 20/09/2018 ዓ/ም ከ4፡00-6፡00
|
ለመጃመሪያ ጊዜ
|
||
ፀደይ ባንክ አ/ማ እንጅባራ ዲስትሪክት

