ቁጥር ግጨ 04/2018
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ ቢሮ የአየር ንብረት አያያዝ አፈፃፀም ፕሮግራም /CALM P-4R/ ፕሮግራም ለዞኖች እና ለወረዳዎች ለIBEX አገልግሎት የሚዉሉ 35 ዴስክቶፕ ኮምፒዩተር፣ 1 ፎቶ ኮፒ ማሽን፣ 35 ፕሪንተር እና 15 እስካነር ዕቃዎችን በጋዜጣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ሰለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ድርጅት ማሟላት ያለባቸው፡-
- በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፣ የእቃው አገልግሎቱን ግዥ መጠን ከብር 200,000 (ከሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (የቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 ቀናት ገንዘብ ቢሮ ከሚገኝበት ባሕር ዳር ከተማ ቀበሌ 03 ከዲፓ መስመር ዝቅ ብሎ ቢሮ ቁጥር 101 ወይም 102 በአካል በመቅረብ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻል ሲሆን ሰነዱን ከገዙ በኋላ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት በመስሪያ ቤቱ ለዚህ ጉዳይ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የገዙትን የጨረታ ሰነድና አስፈላጊ ሰነዶችን በፓስታዎች በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ይዘጋና በዚሁ ዕለት 4፡30 ላይ ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባሕር ዳር ከተማ በሚገኘው የአብክመ ገንዘብ ቢሮ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 ላይ ይከፈታል፡፡
- ጨረታው ሲከፈት የተወዳዳሪ ድርጅቶች ባለቤቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም በቢሮው የጨረታ ገምጋሚ ኮሚቴዎች የጨረታ ሳጥኑ የሚከፈት መሆኑን እየገለጽን በ16ኛው ቀን በዓል ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይዘጋና ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ለተወዳደሩበት እቃ አገልግሎት ብር 80,000 (ሰማኒያ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ በጨረታው ፓስታ ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋጅበት ቋንቋ በአማርኛ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የሚገዙ እቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ሙሉ ስፔስፊኬሽን)፣ መመሪያዎችና የውል ቃሎችን እንዲሁም የዋጋ መሙያ ቅጾችን ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተዘጋጅተው የቀረቡ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ለበለጠ መረጃ፡- አብክመ ገንዘብ ቢሮ ቢሮ ቁጥር 108 በአካል በመገኝት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 13 56 /058 220 08 39 በመደወል ማብራሪያ ማግኝት ይችላሉ፡፡
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ ቢሮ

