የሐራጅ ቁጥር ዳባ/ባዳዲ/0196/26
ዳሽን ባንክ አማ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 1147/2011 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት የሚከተለዉን የተበዳሪ ወይም አስያዥ ንብረት ባለበት ሁኔታ በሐራጅ ይሸጣል፡፡
| ተ.ቁ | የተበዳሪዉ ስም | አበዳሪዉ ቅርንጫፍ | የአስያዥ ስም
|
ቤቱ ሚገኝበት አድራሻ | የንብረቱ አይነት | የጨረታ መነሻ ዋጋ | ጨረታው የሚካሄድበት | |||||
| ከተማ | ቀበሌ | የካርታ ቁጥር | የቦታው ስፋት | |||||||||
| ቀን | ሰዓት | |||||||||||
| 1 | የሽ እርቄ ጥሩነህ | ደብረ ታቦር | እመቤት ጥሩነህ አበጋዝ | ደብረ ታቦር | 04 | 8.2/315/5087/07 | 200 ካሜ | የመኖሪያ ቤት | 2,623,949 | ሰኔ 09/2018 ዓ.ም | 4:00-6:00 | |
| 2 | ኤፍሬም ደሳለን አንተነህ | ባሕር ዳር | ተበዳሪው | ባ/ዳር | 14 | 2/30470/120 | 200 ካ.ሜ G+3 | የመኖሪያ ቤት | 9,824,280 | ሰኔ 03/2018 | 4:00-6:00 | |
ማሳሰቢያ፡-
- ተጫራቾች የጨረታዉን መነሻ ዋጋ 25 በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ በዳሸን ባንክ ስም በተዘጋጀ የባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) በጨረታዉ ዕለት ይዘዉ በመቅረብ መመዝገብ ይችላሉ፡፡
- ጨረታዉ በሰንጠረዥ ላይ በተገለፀዉ ቀን እና ሰዓት ቤቱ በሚገኝበት አድራሻ ይካሄዳል፡፡
- ለመንግስት የሚከፈል ግብር፣ ታክስ፣ ዉዝፍ የሊዝ ክፍያ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስን እና ሌላም ከስም ዝዉዉር ጋር የሚገናኙ ወጭዎችን ገዥዉ ይከፍላል፡፡
- የጨረታዉ አሸናፊ ደብዳቤ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ዋጋ በ15 ቀናት ዉስጥ አጠናቆ መክፈል ይኖርበታል፡፡ ባይከፍል ግን ጨረታዉ ተሰርዞ ያስያዘዉ የሲፒኦ ገንዘብ አይመለስለትም፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሜ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየዉ የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡ በጨረታዉ ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት (ሲፒኦ) ወዲያዉኑ ይመለስላቸዋል፡፡
- በጨረታዉ ላይ አስያዥና ተበዳሪዉ ወይም ህጋዉ ወኪሎቻቸዉ መገኘት ይችላሉ፡፡ ባይገኙም ጨረታዉ በሌሉበት ይካሄዳል፡፡
- ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች የጨረታዉ አሸናፊ ነዉ የሚባለዉ አሸናፊነቱን የሚገልጽ ደብዳቤ በፅሁፍ ሲደርሰዉ ብቻ ነዉ፡፡
- የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጅ መዝጊያ 10 ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል፡፡
- ጨረታዉ ተጀምሮ በተቀመጠዉ ሰዓት ዉስጥ ካልተጠናቀቀ ሊራዘም ይችላል፡፡
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 320 97 81 ደዉሎ መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ዳሸን ባንክ አ.ማ

