ደም ያቃባዉ ባለኬክ ክሬም ድግስ

0
12

በህንድ ላንድሻህር ከተማ በሚገኝ የስፖርት ማሰልጠኛ አዳራሽ በሚያከብረው የልደት በዓሉ ላይ ፊቱን የኬክክሬም ከቀቡት ጓደኞቹ ጋር የተጋጨው ወጣት ወደ ቤቱ አምርቶ የጦርመሣሪያ ይዞ በመመለስ ሦስቱን ተኩሶ መግደሉን ኦዲቲ ሴንትራል ድረ ገጽ አስነብቧል፡፡

የዓይን እማኞችን ገለፃ ዋቢ አድርጐ ድረ ገጹ እንዳስነበበው የ33 ዓመቱ ጂቱ ከአማርዲኘ ሳኒ፣ ማኒሽ ሳኒ እና አካሽ ሳኒ ጋር ፊቱን የኬክ  ክሬም በመቀባታቸው ተበሳጭቶ ጠብ ይገጥማል፡፡ ከዚያም ጠቡይከርና ወደ መኖሪያ ቤቱ ገስግሶ ከጥቂት ጓደኞቹ ጋር የጦር መሳሪያ ይዘው ይመለሳሉ፡፡

 

ጥቃት ፈፃሚዎቹ የባለልደቱን ፊት የኬክ ክሬም የቀቡትን ወጣቶች ምሽት ላይ አፈላልገው እንዳገኛቸውም ጂቱ ተኮሰባቸው፤ ገደላቸውም፡፡

ከሟቾቹ የአንዱ ወንድም ሳንጃይ ሳኒ ቃለመጠይቅ ላቀረበለት ጋዜጠኛ እንደተናገረው በእለቱ ባለልደቱ ወደሱ ስልክ ደውሎ ክብር የጐደለው ፀያፍ ቃላት እንደተናገረው ገልፆለታል፡፡ ሳንጃይም አድረው  ጠዋት በንግግር እንደሚፈቱት ቃል ገብቶለት ለማረጋጋት ጥረት ማድረጉን ነው ያስረዳው፡፡

 

የሁነቱ መቋጫ ግን የዚያችን እለት ምሽት መሻገር አልቻለም፤ አመሻሽ ላይ ጂቱ ሳኒ የሦስቱን ህይወት በጥይት ተኩሶ ቀጥፎ መሰወሩ ለፖሊስ ሪፖርት ይደርሰዋል፡፡

ፖሊስ በቦታው ደረሶ መረጃዎችን አሰባስቧል፡፡ ከተመቱት የሁሉቱ ወዲያው ህይወታቸው መለፉንና አንዱ ሆስፒታል ደርሶ መሞቱን አረጋግጧል፡፡

የፀቡ መነሻ እና ፈፃሚ ጂቱ መሰወሩን እና በቁጥጥር ስር ለማዋል ፍለጋው መቀጠሉንም ድረ ገጹ አስነብቧል፡፡

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የግንቦት 3 ቀን 2018 ዓ.ም  ዕትም

በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘወትር ሰኞ የምትታተመውን የበኲር ጋዜጣን ሙሉ ፒዲኤፍ

በhttp:// www.ameco.et/Bekur

በቴሌግራም – https://t.me/bekur123 ላይ ማግኘት ይችላሉ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here