ቴብል ማውንቴን ብሔራዊ ፓርክ

0
14

ብሔራዊ ፓርኩ በደቡብ አፍሪካ ደቡብ ምእራብ ቀጣና ነው የሚገኘው፡፡ ፓርኩ በ1998 እ.አ.አ የተመሰረተ ሲሆን 221 ኪሎ ሜትር ስኩዌር ተለክቷል፡፡ ፓርኩ የሚገኝበት ከፍታ 1086 ሜትር ሲሆን ኬፕታዎን እና ቴብል ሰርጥን የሚያስቃኝበት ጫፍ ነው፡፡ በዚህ ቦታ በእግር፣ በተሽከርካሪ ወይም በገደሎች ጫፍ በታሰረ ወፍራም ሽቦ ገመድ ላይ በመንሸራተት፣ በመጓጓዝ ቀጣናውን መቃኘት ያስችላል፡፡

በብሄራዊ ፓርኩ የሚገኙ እንስሳት አካባቢውን የተላማዱ ናቸው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ የአጋዘን ዝርያዎች፣ “ክሊፕስሪንገር፣ ኤላንድ፣ ቦንትቦክስ፣ ኬፕማውንቴን ዜብራ” የመሳሰሉ ይገኙበታል፡፡

 

ከእፅዋት የ “ፊንቦስ” ቁጥቋጦ በብዛት ይገኝበታል፤ በየ15 ዓመቱም በእሳት መቃጠል ያለበት ዝርያ ነው – ይህም እንደገና በቅሎ እየታደሰ ለምለም ሆኖ መቆየት የሚያስችለው በመሆኑ ነው የሚቃጠለው፡፡

ከአእዋፍት ብዛታቸው ሦስት ሺህ የሚጠጉ “ፔንጉዊንስ” በስፋት መገኘታቸው ቀጣናውን ልዩ ያደርገዋል፡፡

ፓርኩ የውኃ አካል ዓሳ ነባሪ፣ “ሃምፕ ባክ ሁዌል” ንስር በጐብኚዎች ተመራጭ ቀጣና ነው፡፡

 

ፓርኩን ዝነኛ ካደረጉት መካከል በተወጠረ የብረት ገመድ ላይ መጓጓዥ እና በእግር መንቀሳቀሻ ሞንገድ መኖሩ ተጠቃሽ ነው፡፡

ፓርኩ ጥንታዊ እድሜ ጠገብ የአፍሮ መንታና ደን የለበሰ በመሆኑ ቀጣናዋን ለተላመዱ የዱር እንስሳት መጠለያ ሆኗቸዋል፡፡

ፓርኩን ለመጐብኘት ከታህሳስ እስከ የካቲት ያሉ ደረቅ ወራት እንዲሁም ከሰኔ እስከ ነሀሴ ያሉ ዝናባማ ወራት ተመራጭ መሆኗቸው ነው በማጠቃለያነት የተጠቀሰው፡፡

ለዘገባችን በመረጃ ምንጭነት ሳውዝ አፍሪካ ዶትኔት፣ ሪዘርቭ ዶት ሲኦ፣ እንዲሁም ሳውዝ አፍሪካ ስፔሻሊስት ድረ ገፆችን ተጠቅመናል፡፡

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የግንቦት 3 ቀን 2018 ዓ.ም  ዕትም

በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘወትር ሰኞ የምትታተመውን የበኲር ጋዜጣን ሙሉ ፒዲኤፍ

በhttp:// www.ameco.et/Bekur

በቴሌግራም – https://t.me/bekur123 ላይ ማግኘት ይችላሉ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here