በአብክመ በባሕር ዳር ከተማ ቀበሌ 15 በሚገኘው መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ. ሎት 1. ሰርገኛ ጤፍ ብዛት ሶሰት ሺህ ለሶሰተኛ ጊዜ እና ሎት 2. ነጭ በቆሎ ብዛት አስር ሺህ ለሁለተኛ ጊዜ በግልጽ ጨረታ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ካላቸው አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሁሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ጋራቲ (ዋስትና) ወይም (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ ደረሰኙ ከዋጋ ማቅርቢያ ፖስታው ውስጥ በማስገባት ማያያዝ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ዋጋ የሚሆን ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) እንዳይሰበሰብባቸው ፈቃድ የተሰጣቸው (በግብር አዋጁ ከግብር ነጻ ከሆኑ) አቅርቦቶች ካልሆኑ በስተቀር በግዥው የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም በማድረግ እና ለጨረታው የሚያስፈልጉ ሰነዶች በፖስታው ውስጥ ማስገባትና ፖስታው ላይ ክብ ማህተም በማድረግ በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡
- በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 350 (ሶስት መቶ ሀምሳ ብር) የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ7 ተከታታይ ቀናት ከዩኒየኑ ሒሳብ ክፍል ወይም ቢሮ ቁጥር 101 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ7 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እሰከ 7ኛው ቀን እሰከ 8፡00 ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፓስታ ሳጥን ውስጥ ማሰገባት ሲኖርባቸው በ7ኛው ቀን በ8፡00 ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል፡፡
- ቅዳሜ ለዩኒየኑ የስራ ሰዓት ሲሆን ጨረታው በሚከፈትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በዚሁ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ጨረታው ተወዳዳሪዎች (ተወካዮቻቸው) በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተወዳዳሪዎች ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡
- የጨረታ አሽናፊው በጨረታ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ አሽናፊው የውል ማስከበሪያ ተቀባይነት ባላቸው የዋስትና ዓይነቶች የጠቅላላ የውሉን ዋጋ 10 በመቶ በማስያዝ ውል መፈጸም አለበት፡፡
- አሸናፊው የአሸነፋትን እቃ በፍትህ ውል ከተመረመረ (ከተመዘገብ) የምርመራም ሆነ ይምዝገባ ክፍያ አሸናፊው ይከፍላል /ይሸፍናል ሰብሉን ለማንሳት የሚያሰፈልጉ ማንኛውም የወዛደር ማሰጫኛ እና የትራንሰፓርት ወጭዎችን አሸናፊ የሚሽፍን ይሆናል፡፡
- ሰብሉ ሚገኝበት ቦታ ባ/ዳር ከተማ ከዩኒየኑ መጋዝን የሚገኝ ሲሆን ጥራቱን በአካል በማየት መሙላት አለባቸው፡፡ ከሎት ውስጥ መጠኑን ቀንሶ መሙላት አይቻልም፡፡
- ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በዚህ ያልተጠቀሱ ሀሳቦች ቢኖሩ በአብክመ በህ/ስ/ማ/ የግዥና ሽያጭ መመሪያ ቁጥር 58/2015 መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናሉ፡፡
- ለበለጠ መረጃ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 09 11 59 05 34 /09 18 08 26 26 96 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ

