ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
9

የአዴት ሆስፒታል የግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውል የህሙማን የምግብ አገልግሎት ለአንድ አመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ፡- የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች  መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  4. የግዥ መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  7. የሚቀርቡ የምግብ አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔሰፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል አዴት ሆስፒታል ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ከገንዘብ ያዥ ክፍል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአዴት ሆስፒታል በግዥ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 39 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ከግንቦት 17/2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ 1/2018 ዓ.ም ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ጨረታው ሰኔ 2/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ላይ ይታሸጋል፡፡ በዚሁ እለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 3፡00 ይከፈታል፡፡
  11. መ/ቤቱ ከጨረታው 20 በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለ ስለ መስተካከሉ ፓራፍ መደረግ አለበት፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. ለበለጠ መረጃ ቢሮ ቁጥር 39 በአካል ቀርበው ማናገር ይችላሉ፡፡

የአዴት ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here