የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

0
30

ፀደይ ባንክ አማ ያበደረዉን ብድር መመለስ ያልቻሉ ደንበኞች ለብድሩ አመላለስ በመያዣ ያስያዛቸዉን ቤቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ንብረቶች የተቀመጡትን ቅድመ ሁኔታዎች እና ደንቦች የሚያሟሉ ማንኛዉም ሰዉ እንዲጫረቱ እንጋብዛለን፡፡

ተ.ቁ የተበዳሪ ስም የንብረት አስያዥ /መያዣ ሰጭ ስም የንብረቱ መገኛ ቦታ፣ የካርታ ቁጥር እና የቦታዉ አገልግሎት

 

የቦታዉ ስፋት የጨረታ መነሻ ግምት

 

1 አቶ መሀሪ ታምር ልመንህ

 

አቶ መሀሪ ታምር ልመንህ ቁጭ ከተማ 01 ቀበሌ ካርታ ቁጥር 95/2010 የመኖሪያ ቤት አገልግሎት 200 ካ.ሜ 1,675,257.93
2 አቶ ፀሐይ ሽመላሽ ጋሻዉ ትርንጎ ሙላት አለባቸዉ ሽንዲ ከተማ 01 ቀበሌ ካርታ ቁጥር ሽማ 7949/መ/ር/1 የመኖሪያ ቤት

 

175 ካ.ሜ 1,383,482.51

 

ደንቦች እና ቅድመ ሁኔታች፡-

  1. ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋዉን ¼ ኛውን በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ይዘዉ መቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች ለጨረታ ሲቀርቡ ማንነታቸዉን የሚገልጽ መታወቂያ ይዘዉ መቅርብ አለባቸዉ፡፡ ተጫራቹ ድርጅት ከሆነ የሚጫረተዉ ሰዉ ዉክልና የድርጅቱን መተዳደሪያ ደንብ እንዲሁም ድርጅቱ ህጋዊ ሰዉነት ያገኘበትን የምዝገባ የምስክር ወረቀት ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
  3. ለመንግስት የሚከፈል ማንኛዉም ግብር ቫትን ጨምሮ ከቦታዉና ቤቱ ጋር የተያያዘ ክፍያ እንዲሁም ስም ለማዞር የሚወጡ ወጭዎች በተጫራቹ በገዥ የሚሸፈን ይሆናል፡፡
  4. የጨረታ አሸናፊዉ የጨረታ ዉጤቱ በሚመለከተዉ አካል ፀድቆ አሸናፊነቱ በተረጋገጠ በ15 ቀን ዉስጥ ያሸነፈበትን ሙሉውን ገንዘብ ከፍሎ ማጠናቀቅና ቤቱን መረከብ ይኖርበታል፡፡
  5. የጨረታ አሸናፊዉ በ15 ቀን ዉስጥ ያሸነፈበትን ሙሉዉን ገንዘብ ገቢ ካላደረገ ያስያዘዉን ¼ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታዉ እንደገና ይወጣል፡፡
  6. ጨረታዉ ሰኔ 18/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እሰከ 6፡00 ቡሬ ከተማ ከመናኸሪያዉ ወረድ ብሎ ከሚገኘዉ የፀደይ ባንክ ቡሬ ዳሞት ቅርንጫፍ ግራዉድ ላይ ይሆናል፡፡
  7. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለዉ፡፡
  8. ቤቶቹን በባንኩ አማካኝነት መጎብኘት ይችላሉ፡፡
  9. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 775 11 54 ደዉለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ፀደይ ባንክ አ.ማ ፍኖተ ሰላም ዲስትሪክት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here