በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2. የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3. የመኪና መለዋወጫ እቃዎች፣ ሎት 4. የመኪና ዘይት እና ቅባት እንዲሁም ሎት 5. ፕላስቲክ ማዳበሪያ ከረጢት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት እና የሚገዙ እቃዎች ዋጋ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተገለጹትን መስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከሰነዱ ጋር አብረው ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የሚገዙ የእቃ እና ያገልግሎት ግዥ አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውንም ዓይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የጠቅላላ ዋጋዉን አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመስሪያ ቤቱ የገቢ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን እና ደጋፊ ማስረጃቸውን የሚያዘጋጁበት ቋንቋ አማርኛ መሆን አለበት፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ ወይም ለመወዳደር የሚወጡ ወጭዎች ቢኖሩ መ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ተኛው ቀን ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 106/107 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ተኛው ተከታታይ ቀን ቆይቶ በ16ተኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ተዘግቶ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አዳራሽ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ ህዝባዊ በዓል ወይም እሁድ ቅዳሜ ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በራሳቸው ምክንያት ባይገኙ ጨረታዉ በሌሉበት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በተጫራቾች መመሪያ ይዘት ላይ ምንም ዓይነት ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም፡፡
- የገዥ መ/ቤት አድራሻ አ.ብ.ክ.መ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ባሕር ዳር ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 058 218 00 14 /058 218 11 03 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አብክመ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን

