ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
11

የሰሜን ወሎ ዞን ማረ/ቤት መምሪያ ወልድያ ከሃምሌ 1/2018 ዓ.ም እሰከ ሰኔ 30/2019 ዓ.ም ለአንድ ዓመት የሚቆይ ሎት 1. ሰርገኛ ጤፍና የተከካ በቆሎ፣ ሎት 2. ፊኖ ነጭ የዳቦ ዱቄት፣ ሎት 3. የባልትና ውጤቶችና ሎት 4. የተፈለጠ የማገዶ እንጨት የሚያቀርቡ ነጋዴዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ አመት መግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. በዚህው የሥራ መስክ ለመስራት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡
  4. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. አሸናፊው አካል በስማቸው የታተመ ደረሰኝ ያላቸው፡፡
  6. የሚሞላዉ ዋጋ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ ተጫራቾች (ቫት) ተመዝጋቢ መሆን አለባቸዉ፡፡
  7. የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ የሚቆይበት ጊዜ ከግንቦት 17/2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ 01/2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ድረስ ብቻ ነዉ፡፡
  8. የጨረታ ማስከበሪያ አንድ በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ በባንክ የተረጋገጠ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
  9. የጨረታ ሰነዱን ከግንቦት 17/2018 ዓ.ም እስከ 01/10/2018 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ከመ/ቤቱ ዋና ገንዘብ ያዥ የማይመለስ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰንድ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታዉን ሰንድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ እስከ ሰኔ 02/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 3፡30 ድረስ ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀዉ ሣጥን ማስገባት አለባቸዉ፡፡ ጨረታዉ በዚሁ ቀን ሰኔ 02/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 3፡30 ላይ ታሽጎ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ መኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  11. ተጫራቾች ያሸነፋትን እቃዎች በሙሉ በራሳቸዉ ወጭ መ/ቤቱ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  12. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ሙሉ አድራሻ፣ ማህተም ፊርማና ሌሎች ማስረጃዎችን አሟልተዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  13. በጨረታዉ የሚቀርቡ ዕቃዎች በሙሉ ጥራታቸዉን የጠበቁ መሆን አለባቸው፡፡
  14. የጨረታ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች የዉል ማስከበሪያ 10 በመቶ በባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነዉ፡፡

ለበለጠ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 033 331 12 40 በመደወል ወይም በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የሰሜን ወሎ ዞን ማረ/ቤት መምሪያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here