ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
15

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አማካኝነት ለምስ/ደ/ወ/ አስተዳደር /ጽ/ቤት ለ3ኛ ፌዝ ለቢሮ ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ የግንባታ ማቴሪያል ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
  1. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉና ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  1. የጨረታ ሰነድ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. የጨረታ ሰነዱን መግዛት የምትፈልጉ ከግንቦት 17/2018 ዓ/ም ጀምሮ በምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. የግንባታ ማቴሪያል ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን አሸናፊዉ የሚለየዉ በሎት ይሆናል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ከግንቦት 17/2018 ዓ/ም እስከ ሰኔ 1/2018 ዓ/ም ባሉት ተከታታይ ቀናት መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ) ቦንድ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒዩ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ በፖስታ ታሽጎ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ ፡፡
  6. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ሰኔ 2/2018 ዓ/ም በ3፡30 ታሽጎ በግዥ ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 6 ሰኔ 2/2018 ዓ.ም በ4.00 ይከፈታል፡፡
  7. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባይገኙም ለጨረታዉ መሟላት የሚገባቸዉ ሁኔታዎች ከተሟሉ ተጫራቾች በሌሉበት ጽ/ቤቱ የጨረታዉን ፖስታ የመክፈት ስልጣን አለዉ፡፡
  8. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  9. ተጫራቾች በጨረታዉ ማሸነፈቸዉ እና የዉል ስምምነት እንዲፈጽሙ በተገለጸበት ጊዜ ካሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የዉል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒዩ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ማስያዝ እና ንብረቱን ምስ/ደ/ወ/ አሰተዳደር ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግና የጫኝና አዉራጅ በተጫራቹ የሚሸፈን መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  10. የግንባታ ቁሳቁሱን የምንረከበዉ በላብራቶሪ ተፈትሾ  ሲያልፍ ብቻ ነዉ፡፡
  11. ስለ ጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር  058 335 0632 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡-ከዚህ በፊት በየትኛዉም ደረጃ በነበራቸዉ የአፈጻጸም ችግር ምክንያት የታገዱ አቅራቢዎችን አይመለከትም፡፡

 

የምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here