በአፈ/ከሳሽ ሜሮን ተድላ እና በአፈ/ተከሳሽ አዱኛ ታየ መካከል ስላለው የገንዘብ ክስ ጉዳይ የአፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ በቡሬ ከተማ 03 ቀበሌ በአዋሳኝ ምሥራቅ ፀሐይ አለማየሁ፣ በምዕራብ ወልደልዑል ጌጤ፣ በሰሜን መንገድ እንዲሁም በደቡብ ሀይማኖት ይሁን መካከል ተዋስኖ የሚገኘው መኖሪያ ቤት ለፍርድ ማስፈፀሚያ በፍ/ቤት ጨረታ እንዲሸጥ የተወሰነ ስለሆነ በመነሻ ዋጋ ብር 3,385,478.75 (ሶስት ሚሊዮን ሶስት መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ አራት መቶ ሰባ ስምንት ብር ከሰባ አምስት ሳንቲም) ሰኔ 19/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 እንዲሸጥ ሲል ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
የየፍኖተ ሰላም ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት

