በአፈ/ከሣሽ 1ኛ. ድንበሩ አቻም፣ 2ኛ, ንጉሴ ልመንህ፣ 3ኛ, የማታው በየነ እና በአፈ/ ተከሣሽ ሞሴ ታመነ መካከል ስላለው የዕቁብ ገንዘብ ክስ ክርክር ጉዳይ በአንጅባራ ከተማ ቀበሌ 04 በምሥራቅ እውነቱ ታመነ፣ በምዕራብ ደረጀ አየሁ፣ በሰሜን መንገድ የሚያዋስነው የአፈጻጸም ተከሣሽ መኖሪያ ቤት በመነሻ ዋጋ ብር 2,900,000 (ሁለት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሺህ ብር) በጨረታ ይሸጣል፡፡ የጨረታ ማስታወቂያው ከሰኔ 01/2018 እስከ ሰኔ 30/2018 ዓ/ም ለ30 ቀን በጋዜጣ የሚውል ሲሆን ጨረታው የሚካሄድበት ቀን ከሐምሌ 01/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ነው፡፡ መግዛት የሚፈልጉ ሁሉ የጨረታ መነሻ ዋጋዉን 1/4ኛዉን ብር በማስያዝ በቦታው ተገኝቶ መጫረት የሚችሉ መሆኑን ፍ/ቤቱ ያስታውቃል፡፡
የአዊ ብሔ/አስ /ከፍ/ፍ/ቤት

