የደ/ታቦር ከተማ መሬት መምሪያ የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 መሰረት በ2018 በጀት ዓመት 3ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ለመኖረያ የሚውሉ ቦታዎችን በመሬት ሊዝ በጨረታ ለተጫራቾች ማስተሳሰር ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡-
- ጨረታው ከሰኔ 01/10/2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ 12/2018 ዓ.ም ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀን በጋዜጣ ይቆያል፡፡ መጫረት ለሚፈልጉ የጨረታ ሰነዱን ደ/ታቦር ከተማ መሬት መምረያ ቢሮ ቁጥር 22 ድረስ በመምጣት እና በመመዝገብ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ቀን ከሰኔ 01/2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ 12/2018 ድረስ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በመንግስት የሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 የደ/ታቦር ከተማ መሬት መምሪያ ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋው ሰኔ 12/2018 ዓ/ም በ11፡00 ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ሰኔ 13/2018 ዓ/ም 3፡00 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደ/ታቦር ከተማ መሬት መምሪያ ግቢ ውስጥ ነው፡፡
- ሁሉም ተጫራቾች በፖስታ አሽገው ማስገባት ያለባቸው የሀሳብና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ፣ በባንክ የተረጋገጠ የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ (ሲፒኦ) ለድርጅት 15 በመቶ እና ለመኖሪያ 20 በመቶ የተከፈለበት እና ኦርጅናል (ዋናውን) ሰነድ የገዙበት ደረሰኝ ናቸው፡፡
- የጨረታ ቦታዎችን ብዛት እና ሳይት ኘላን በውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ መመልከት ይችላሉ፡፡
- መስሪያ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የደ/ታቦር ከተማ መሬት መምሪያ

