የቢቡኝ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት አመት ሎት 1. የእንስሳት መድሀኒት፣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ሰለዚህ ለመጫረት የሚፈልጉ ሁሉ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በአዲሱ አዋጅ መሠረት የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ የሙያ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥ መጠኑ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ለየብቻዉ በማሸግና በእያንዳንዱ ፖስታ ላይ የግዥ ፈፃሚ መስሪያ ቤትና የተጫራቹን ሙሉ ስምና አድራሻ ፊርማና ማህተም በማስቀመጥ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- አሸናፊ ተጫራች ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ የጨረታ አሸናፊዉ የዉል ማስከበሪያ ጠቅላላ ዋጋውን 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
- የሚቀርቡት የእንስሳት የመድሃኒት ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) የማይመለስ ከፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 12 በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ብር 20,000 (ሀያ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሃሳባቸዉን ዋናውንና ቅጁን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በቢቡኝ ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥ/ን/አ ቡድን ቢሮ ቁጥር 01 በተዘጋጀው የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ሰኔ 1/2018 ዓ/ም እስከ ሰኔ 15/2018 ዓ/ም 11፡30 ድረስ መግዛት እና ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሉቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በግዥ /ንአስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 01 ለዕቃ አቅርቦት በ16ኛዉ ቀን ሰኔ 16/2018 ዓ.ም 3፡00 ይታሸጋል፡፡ በዚሁ ቀን 3፡30 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን መ/ቤቱ 20 በመቶ የመጨመር የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታዉ በሚከፈትበት ቀን ብሄራዊ የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቀን ይከፈታል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 1 ድረስ በአካል በመገኘት መረዳት ይችላሉ፡፡
የቢቡኝ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

