የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች ያሉትን ክፍት የስራ መደቦች ዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታውን ከሚያሟሉ ስራ ፈላጊዎች መካከል በቋሚ ቅጥር
አወዳድሮ በመቅጠር ማሰራት ይፈልጋል፡፡
| ተቁ | የሥራ መደቡ መጠሪያ | ደረጃ | የመ/መ/ቁ | ደመወዝ | ብዛት | ዳይሬክቶሬት/ዝግጅት | የሥራ ቦታ | ተፈላጊ የትምህርት ዝግጅት | ተፈላጊ የስራ ልምድ |
| 1. | አረብኛ ቋንቋ ከፍተኛ ሪፖርተር 2
|
12 | አሚ-1525
|
በኮርፖሬሽኑ የደመወዝ ስኬል መሠረት | 01 | አዲስ አበባ ኅብር ዝግጅት | አዲስ አበባ | በብሮድካስት ጋዜጠኝነት ፣በጋዜጠኝነትና ተግባቦት፣(ኮሞኒኬሽን)፣ ስነጽሁፍ ፣በቋንቋ፣ፖለቲካል ሳይንስ ዓለም አቀፍ ግንኙነትና በተዛማጅ የትምህርት መሰክ የሰለጠነ | የመጀመሪያ ድግሪና 3 ዓመት ወይም ሁለተኛ ዲግሪና 1 ዓመት አግባብነት ያለው የስራ ልምድ ከአማርኛ በተጨማሪ የአረብኛ ቋንቋ መስማት፣መናገር ፣ማንበብና መጻፍ የሚችል፡፡
|
| 2. | አፋርኛ ቋንቋ ከፍተኛ ሪፖርተር 2 | 12 | አሚ-1500 | በኮርፖሬሽኑ የደመወዝ ስኬል መሠረት | 01 | አዲስ አበባ ኅብር ዝግጅት | አዲስ አበባ | በብሮድካስት ጋዜጠኝነት ፣በጋዜጠኝነትና ተግባቦት፣ተግባቦት(ኮሞኒኬሽን)፣ ስነጽሁፍ ፣በቋንቋ፣ፖለቲካል ሳይንስ ዓለም አቀፍ ግንኙነትና በተዛማጅ የትምህርት መሰክ የሰለጠኑ፡፡ | የመጀመሪያ ድግሪና 3 ዓመት ወይም ሁለተኛ ዲግሪና 1 ዓመት አግባብነት ያለው የስራ ልምድ ከአማርኛ በተጨማሪ አፋርኛ ቋንቋ መስማት፣መናገር ፣ማንበብና መጻፍ የሚችሉ፡፡
|
ማሳሰቢያ፡-
- የምዝገባ ቀን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ለ7 ተከታታይ የስራ ቀናት ይሆናል፡፡
- አመልካቾች ለፈተና በሚቀርቡበት ጊዜ ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ፣ የትምህርት ማስረጃቸውን ኦርጅናል ከማይመለስ ኮፒ ጋር ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- አመልካቾች በእምነት ማጉደል በማጭበርበር ወይም በስርቆት ወንጀል ተከሰዉ ከሆነ ስልጣን ባለዉ አካል ተፈርዶባቸዉ የመቀጠር መብታቸዉን እንዲጠቀሙ ስልጣን ያለዉ ፍርድ ቤት የወሰነበትን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ከተጠቀሰዉ አግባብነት ያለው የትምህርት ዝግጅት ውጭ ለምዝገባ የሚቀርቡ ሌሎች ማስረጃዎች ተቀባይነት አይኖራቸዉም፡፡
- አመልካቾች መልካም ስነ-ምግባር ያላቸው፣ ከማንኛውም ደባል ሱስ የፀዱ፣ጥሩ ስብዕና ያላቸው፡፡
- ተወዳዳሪዎች በተመዘገቡበት የስራ መደብ ለምን ተቀጥረው መስራት እንደፈለጉ በጽሁፍ ገልፀው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- አመልካቾች የሙያ ብቃት በሚያስፈልጋቸው የት/ት ዝግጅት የብቃት ማረጋገጫ በማስታወቂያው በተጠየቀው የት/ት ደረጃ ልክ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የሙያ ብቃት ምዘና ያልተጀመረባቸው የትምህርት መስኮች ከሚመለከተው ተቋም የሙያ ብቃት አለመጀመሩን ማስረጃ ካቀረቡ መመዝገብ ይችላሉ፡፡
- በግል የተሰራባቸው የሰራ ልምዶች የሰራ ግብር የተከፈለበት ማስረጃ ከገቢዎች ጽ/ቤት ማቅረብ ይገባል፡፡
- ከአንድ የስራ መደብ በላይ መመዝገብ አይቻልም፡፡
- የፈተና ቦታና ፈተና የሚሰጥበት ቀን በሌላ ማስታወቂያ ይገለፃል፡፡
- አመልካቾች የምትመዘገቡበት ሊንክ በዌብሳይታችን amharaweb.com ማግኘት ትችላላችሁ ወይም https://forms.gle/WduRr5oxMNHw6JHn7 መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳስባለን፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 226 5007 ይደዉሉ፡፡
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን
ባህር ዳር

