የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

0
10

ወ/ሮ እመቤት ቸኮል ከፀደይ ባንክ ይልማና ዴንሳ ቅርንጫፍ የተበደሩትን ገንዘብ መመለስ ስላልቻሉ ለብድሩ አመላለስ በዋስትና የተያዘውን በመያዣ ሰጭ በአቶ አየነው አንዱዓለም ስም የተመዘገበ አድራሻው በይልማና ዴንሳ ወረዳ በአዴት ከተማ ቀበሌ 03 በካርታ ቁጥር ከአገ/2160/2008 የቦታው ስፋት 180 ካ/ሜ የሆነ አዋሳኙም በሰሜን ይበልጣል መንጌ፣ በደቡብ ቻለው መራ፣ በምሥራቅ መንገድ እንዲሁም በምዕራብ የኔአያል አቻሜለህ የሚያዋስነውን መኖሪያ ቤት በመነሻ ዋጋ ግምቱ ብር 1,004,066.91 (አንድ ሚሊዮን አራት ሺህ ስልሳ ስድስት ብር ከዘጠና አንድ ሳንቲም) ባንኩ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ከላይ የተገለፀውን ንብረት ከዚህ በታች የተቀመጡትን ቅድመ ሁኔታዎች እና ደንቦች የሚያሟሉ ማንኛውም ሰው እንዲጫረት እንጋብዛለን፡፡

  1. ጨረታው የሚካሄደው ሀምሌ 09/2018 ዓ/ም በፍኖተ ሰላም ከተማ በፀደይ ባንክ ፍ/ሰላም ዲስትሪክት ከህንፃው ሥር ከጥዋቱ 3፡00 – 6፡00 ይሆናል፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ ተኛውን በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ይዘው መቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች ለጨረታ ሲቀርቡ ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡ ተጫራቹ ድርጅት ከሆነ የድርጅቱን መተዳደሪያ ደንብ፣ የተወካዩን ሰው ውክልና እና ድርጅቱ ህጋዊ ሰውነት ያገኘበትን የምዝገባ የምስክር ወረቀት ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
  4. ለመንግስት የሚከፈል ማንኛውም ግብር ቫትን ጨምሮ ከቦታውና ከቤቱ ጋራ የተያያዘ ክፍያ እንዲሁም ስም ለማዛወር የሚወጡ ወጭዎች በተጫራች (በገዥ) የሚሸፈን ይሆናሉ፡፡
  5. የጨረታ አሸናፊው የጨረታ ውጤቱ በሚመለከተው አካል ፀድቆ አሸናፊነቱ በተረጋገጠ በ15 ቀን ውስጥ ያሸነፈበትን ሙሉውን ገንዘብ ከፍሎ ንብረቱን መረከብ አለበት፡፡ ገንዘቡን ገቢ ካላደረገ ያስያዘውን 1/4 ኛ የጨረታ ማስከበሪያ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው እንደገና ይወጣል፡፡
  6. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን የመሰረዝ መብት አለው፡፡
  7. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 775 11 54 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ፀደይ ባንክ ፍኖተ ሰላም ዲስትሪክት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here