ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
20

የቡሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2019 በጀት ዓመት ዓመታዊ ውል በመያዝ ሎት 1. ለተኝቶ ህክምና ታካሚዎች አገልግሎት የሚዉል የበሰለ ምግብ አቅርቦት በሆቴሎችና ካፍቴሪያ ዘርፍ ፈቃድ ላላቸው ግለሰቦች ማስቀረብ እና ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ ጥገና በግልጽ ጨረታ አውጥቶ ማሰራት እና ለምግብ ተጫራቾች ደግሞ የሆስፒታሉን ካፍቴሪያ በብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) ብቻ ማከራየት እና ማስቀረብ ይፈልጋል፡፡ በካፌው የሚቀርቡ አገልግሎቶች፡- የተለያዩ  ምግብ  አይነቶችን፣ የተለያዩ አይነት ትኩስ  መጠጦች የጀበና  ቡናን   ጨምሮ፣ የተለያዩ  አይነት   ቀዝቃዛ መጠጦችን ከአልኮል  ወጭ፣ መቀመጫ ወንበር እና ጠረጴዛ በራሱ ማቅረብ የሚችሉ፣ የሻይ ማሽን ፣ፍሪጅ፣ ቴሌቨዥን እና ሌሎች   ቁሳቁሶችን   አሸናፊ  ተጫራች ያቀርባል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
  2. የግብር ክፍያ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉ፡፡
  3. የግዥ መጠኑ ከብር 200,000 እና ከዚያ በላይ ከሆኑ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡ ነገር ግን ከላይ ከ1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታው ውጭ ይሆናል፡፡
  5. የሚሰሩ ሥራዎች፣ የሚቀርቡ የምግብ እና የመጠጥ አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ከግ/ፋ/ንብ/አስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 63 ማግኝት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ብር ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማሲያዝ ይችላሉ፡፡
  8. ማንኛዉም ተጫራቾች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸጉ ፖስታዎች በቡሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 63 በተዘጋጀዉ ሳጥን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ 16ኛው ቀን 2፡59 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  9. ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉን በተገኙበት በቡሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ውስጥ የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በግ/ፋ/ን/አስ/ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 63 በ16ኛው ቀን 3፡00 ታሽጎ 3፡30 በይፋ ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በዓል ወይም እሁድ ቅዳሜ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሸጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. የጨረታው አሸናፊ ከተለየ በኋላ በሚቀጥሉት 5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ ካሸነፈው ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በማስያዝ ውል መያዝ ይኖርበታል፡፡
  11. ከተጨማሪ እሴት ታክስ በፊት ብር 20,000 (ሃያ ሽህ ብር) እና በላይ ከተፈጸመ ዊዝ ሆልዲንግ ታክስ 3 በመቶ ይቀነሳል፡፡
  12. ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በግ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 63 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 774 0576 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  13. የጨረታው አሸናፊ መሆን የሚችለው በተጫረተበት ዘርፍ በጥቅል ዋጋቸው ዝቅተኛ ዋጋ የሞላውን በመምረጥ ነው፡፡
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡ ሆኖም ጨረታዉ በመሰረዙ ምክንያት ተጫራቾች ላወጡት ዋጋ ሆስፒታሉ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
  15. ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በግ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 63 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 774 0576 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡-

  • ተጫራቾች የካፌዉን  እና  የተኝቶ  ታካሚዎችን  ምግብ  ተለይቶ  መሙላት  አለበት፡፡
  • የካፌዉ ወርሐዊ   ኪራይ ብር 10,000 ሲሆን  የሚቀርበው    ምግብ እና  መጠጥ  በጨረታ   ሰነዱ ላይ   የተገለፀው   መሆን   አለበት፡፡
  • መብራት እና  ዉሃ በሆስፒታሉ ካለ የሚቀርብ ሆኖ በማይኖርበት  ጊዜ  አሸናፊዉ ገዝቶ  የሚጠቀም  ይሆናል፡፡
  • ለካፍተሪያዉ እንዲቀርቡ ከተዘረዘሩት የምግብና የመጠጥ  ዓይነቶች  በተጨማሪ ከአልኮል ዉጭ በተመጣጣኝ  ዋጋ ማቅረብ ይችላል፡፡

የቡሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here