የአብክመ ገቢዎች ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት በeTAS በጀት Advanced CI/CD Technical Training for IT Experts አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከላይ የተጠቀሰውን ዕቃ ለማቅረብ የሚችሉና ህጋዊ የአቅራቢነት ፈቃድ ያላቸው አቅራቢዎች ሁሉ በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት የሚያቀርቡ እና ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይ ለሚጠይቁ ግዥዎች የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር Advanced CI/CD Technical Training for IT Experts ብር 40,000 (አርባ ሺህ ብር) ብቻ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተመሰከረለት ቼክ (ሲፒኦ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት አብክመ ገቢዎች ቢሮ ቁጥር 313 Advanced CI/CD Technical Training for IT Experts የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ብቻ ሰነዱን በመግዛት የነጠላ ዋጋ እና ጥቅል ዋጋ በመሙላት በፖስታ በማሸግ ቢሮ ቁጥር 313 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ቅዳሜ እስከ 6፡30 ጨምሮ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 313 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ቢሮው ጨረታውን የመክፈት መብት አለው፡፡ ሁኖም 16ኛዉ ቀን ቅዳሜ ፣እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰዉ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ማንኛውንም ወጭ ራሱ ችሎ ለቢሮው አሸናፊ የሆነባቸውን ዕቃዎች ያስረክባል፡፡
- ቢሮዉ በማንኛውም ሰዓት ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- አድራሻችን፡- ባሕር ዳር ቀበሌ 16 ሜድሮክ ጀርባ እና የድሮው ዶ/ር ፍሬው የነበረው የአሁኑ ዶ/ር አዲሱ ፊት ለፊት ስልክ ቁጥር 058 226 57 65 ወይም 058 226 61 71 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የአብክመ ገቢዎች ቢሮ

