ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
29

በሰሜን ወሎ ዞን የጉባላፍቶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በተዘዋዋሪ /ሪቬልቪግ ፈንድ በጀት፣ በስፖርት ምክር ቤት በጀት እና GCF /ግሪን  ክላይሜት ፈንድ በጀት  ሎት 1. የእንስሳት መድሃኒት፣ ሎት 2. የስፖርት ማቴሪል እንዲሁም ሎት 3. ኤሌክትሮኒክ  እቃ  በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

  1. የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውና የቫት ተመዝጋቢ ስለመሆናቸዉ የምስከር ወረቀት  ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች ያሸነፉትን ሎት በተሰጠው (ስፔስፊኬሽን መሰረት በማቅረብና ማጓጓዣ፣ የመጯኛና የማዉረጃ ወጭዉን በራሳቸዉ መሸፈን አለባቸዉ፡፡  ሁሉንም  ንብረቶች  በጉባላፍቶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በሚገኙ ንብረት ክፍሎች ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው በኋላ በ5 ተከታታይ ቀናት ውል በመውሰድ እና በውሉ ላይ በተቀመጠው ቀነ  ገደብ  ውስጥ ሁሉንም ያሸነፉበትን  እቃዎች ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች ከሚያቀርቧቸው  ሰነዶች ላይ የድርጅታቸው ማህተም ስምና ፊርማ በሚነበብ መልኩ  መፃፍና በየገፁ ማህተም ማድረግና መፈረም ይጠበቅባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ኦርጅናል እና ከፒ ማድረግ  በየሎቱ በፖስታ አሽገው ማቅረብ እና በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ውድድሩ በጠቅላላ ድምር ዋጋ በሎት መሆኑ ታውቆ በየሎቱ የተዘረዘሩትን እቃዎች ዋጋ ሁሉንም መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች ስለሚያቀርቧቸው እቃዎች ትክክለኛነቱን እና በተጠየቀው (ስፔስፊኬሽን) መሰረት ስለመቅረቡ በጥራት አረጋጋጭ ባለሙያ ተረጋግጦ መስሪያ ቤቱ የሚረከብ ይሆናል፡፡
  8. የጨረታ ሰነዱን በሰሜን ወሎ ዞን በጉባላፍቶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን በመምጣት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመከፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን ከነማስወረጃዎቹ በታሸገ ፖስታ በድርጅትዎ ማህተም ተረጋግጦ ይህ የጨረታ  ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ  ሁሉም  ሎቶች  ለተከታታይ 15 ቀን ቆይተው በ16 ኛው ቀን 5፡00 ላይ ታሽጎ 5፡30 በግዥ ንብረት አስ/ር ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 ይከፈታል፡፡  ነገር ግን የጨረታ መክፈቻ ቀን በዓል ቀን ከሆነ ወይም የሥራ ቀን ካልሆነ ሁሉም ጨረታዎች ወደ ቀጣይ የሥራ ቀን ተሸጋግሮ  5፡00 ታሽጎ 5፡30ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  10. ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ ላይ ማስተካከያ ጥያቄ ካላችሁ ከጨረታው መክፈቻ ጊዜ ከ5 ቀን በፊት ለጽ/ቤቱ በደብዳቤ ማሳወቅ አለባችሁ፡፡
  11. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ሎት 1. የእንስሳት መድሃኒት 9,000 (ዘጠኝ  ሽህ ብር)፣ ሎት 2. የስፖርት ማቴሪያል 2,000 (ሁለት ሽህ ብር) ሎት 3.  የኤክትሮኒክስ እቃ  5000 (አምስት ሽህ ብር) በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ኦርጅናሉን በጨረታው ፖስታ ውስጥ  ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  12. የጨረታ አሸናፊ ከታወቀ በኃላ አሸናፊው ውል ከወሰደ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ይለቀቃል፤ አሸናፊዉ  የዉል ማስከበሪያ 10 በመቶ በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ እና በሁኔታ ላይ ባለተረጋገጠ የባንክ ዋስትና ኦርጅናሉን በማስያዝ በጉ/ወ/ፍትህ/ጽ/ቤት በኩል ውል መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡
  13. ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃ ሙሉ በሙሉ ሳያስረክቡ ክፍያ ቢጠይቁ ወይም እቃው በገበያ ላይ የለም የሚል ምክንያት መ/ቤቱ አያስተናግድም፡፡ ነገር ግን እቃዎቹን ሙሉ በሙሉ ካስረከቡ ክፍያው ወዲያውኑ ይፈፀማል፡፡
  14. የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኃላ የሚቀርብ ማስረጃና የተሳሳተ የጨረታ ሰነድ ማቅረብ ከጨረታ ውጭ ያደርጋል፡፡
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ማግኘት ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 033 431 07 36 ወይም 033 540 07 21 ደውለው ወይም ጉባላፍቶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ ንብረት አስተዳደር ቡድን በአካል በመምጣት መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የጉባላፍቶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here