ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
114

በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን  የጉና በጌ ምድር ወረዳ የክምር ድንጋይ መሪ ማዘጋጃ ቤት  የከተማ ቦታ በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 እና በሊዝ መመሪያ ቁጥር 1/2005 መሰረት  2018 በጀት ዓመት  1.ኛ ዙር በጨረታ ለመኖሪያ አገልግሎት 8 (ስምንት) ለድርጅት 1 (አንድ) ቦታዎችን ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡

  1. መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) የሥራ ቀናት ከ2፡30 እስከ 11፡30  የማይመለስ ብር 400 (አራት መቶ ብር) በመክፈል  ቢሮ ቁጥር 6 መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. ጨረታው የሚዘጋው በ10 ኛው ቀን በ11፡30 ይሆናል፡፡
  3. ጨረታው የሚከፈተው ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በ3፡00 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በክምር ድንጋይ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት አዳራሽ ይሆናል፡፡
  4. መስሪያ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  5. ቦታውን ለመጎብኘት ከፈለጉ ከጨረታ ኮሚቴ ጋር መጎብኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ሲፒኦ) ለድርጅት 15 በመቶ እንዲሁም ለመኖሪያ 10 በመቶ ህጋዊ ከሆነ ባንክ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ በጽ/ቤቱ የውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳ ወይም በስልክ ቁጥር 09 18 71 44 11 ደውለው መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የክምር ድንጋይ መሪ ማዘጋጃ ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here