የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

0
3

በአፈፃፀም ከሳሽ አፍሪካ ሆቴል እቁብ ማህበር  እና በአፈፃፀም ተከሳሾች እነ ገዳሙ አሳየ አራት እራሳቸው መካከል ስላለው የእቁብ ገንዘብ ክርክር የአፈፃፀም ተከሳሾች የተወሰነባቸውን ገንዘብ ለመክፈል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የአፈፃፀም ተከሳሽ ወ/ሮ ገነት ተፈሪ ንብረት የሆነ በቲሊሊ ከተማ 02 ቀበሌ   በምሥራቅ ክፍት ቦታ፣ በምዕራብ መንገድ ፣ በሰሜን ታደለ መለሰ እንዲሁም በደቡብ አየሁ ምህረት የሚያዋስነው 275 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያለ መኖሪያ ቤት ግምት መነሻ ዋጋ ብር 633,056.67 (ስድስት መቶ ሰላሳ ሶስት ሺህ ሀምሳ ስድስት ብር ከስልሳ ሰባት ሳንቲም) ይሸጣል፡፡ ስለሆነም ከሰኔ 15/2018 እስከ ሀምሌ 15/2018 ዓ.ም ለአንድ ወር  በጋዜጣ ወጥቶ ከቆየ በኋላ ሀምሌ 16/2018 ዓ.ም ከ3፡00 እስከ 5፡00 ባለው ጊዜ ማንኛውም ተጫራች በቦታው በመገኘት እንዲጫረት እና የጨረታ ኮሚቴው በቦታው ተገኝተው  እንዲያጫርቱ፡፡ የጨረታው አሸናፊ ¼ ኛውን ለአጫራቾች ኮሚቴ  እንዲያስይዝ ሲል ፍርድ ቤቱ አዝዟል፡፡

   የጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ፍ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here