ማደናገሪያው “ዳዝል”

0
4

ሩሲያ በአንደኛው የዓለም ጦርነት (1914 እስከ 19) እ.አ.አ የጦር ተሽከርካሪዎቿ በተቃራኒ ኃይል ኢላማ እንዳይታዩ ለማድረግ የተጠቀመችበትን የጥቁር እና ነጭ ቀለም ማደናገሪያ ቅብ አሁን ላይ ከዩክሬን ጋር በምታካሂደው ጦርነት በሰውሰራሽ አስተውሎት (ኤ አይ) የሚሰሩ ድሮኖችን ለመጠበቅ ማዋሏን ኦዲቲ ሴንትራል ድረ ገጽ አስነብቧል፡፡

አሁን በአለንበት ዘመን ዩክሬን ወታደራዊ እንቅስቃሴዋን በተራቀቁ ድሮኖች አና ሮቦቶች ላይ ባደረገችበት ወቅት ሩሲያ በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ተሽከርካሪዎቿ እንዳይለዩ ለማድረግ የተጠቀመችበትን ስልት አሁን ላይ መገልገሏ ነው የተጠቀሰው፡፡ስልቱ በ1917 ከጀርመን የጦር ኃይል ይሰነዘሩ የነበሩ ጥቃቶችን ለማደናገር ወይም ውጤታማነታቸውን ለመቀነስ ኖርማን ዊልሰን በተባለ ጠቢብ ነው የተነደፈው  “ዳዝል” በሚል የሚታወቀው የቅብ ስልት፡፡

ያኔ ከ1917 እስከ 1919 እ.አ.አ የቅብ ስልቱ ከጀርመን ባህር ኃይል ጥቃት ለመጠበቅ የተዘየደ ነበር፡፡ ዛሬ አንድ ምእተ ዓመት ካለፈ በኋላ ሩሲያ ስልቱን ተግባራዊ አድርጋለች – ከዩክሬን ጋር በምታደርገው ጦርነት፡፡

የጦር ስልቱ በሩሲያ በኩል ውጤታማ እንደሆነ ታሳቢ ቢደረግም በዩክሬን በኩል የዜብራው ንድፍ ሩሲያ እንዳሰበችው ሊሰራ እንደማይችል ነው  የተመላከተው – በባለሙያዎች፡፡

የዩክሬን 17ኛ ጦር የሰው አልባ የጦር መሣሪያዎች አዛዥ ሜጀር ማይኮላ ኮሌስኒክ “አርሚ 3” ለተሰኘ መጽሄት  የዩክሬን ጦር የሩሲያ የጦር ተሽከርካሪዎች የፈለገውን ዓይነት የማደናገሪያ ቅብ ቢቀቡም ከመመታት እንደማይድኑ ነው የተናገሩት፡፡

በመጨረሻም በኤሮስፔስ እና ሰውሰራሽ አስተውሎት (ኤ አይ)ባለሙያ የሆኑት ቶድ ኢ ሃምፍሪስ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ለሚሰሩ ድሮኖች ስልቱ ውጤታማ ሊሆን እንደሚችል ነው ያስረዱት፡፡ ያም ሆኖ ዩክሬን በእጅ  የሚታዘዙ ድሮኖችን ልትቀይር  ወይም ተጨማሪ ስልጠና እና በመሣሪያዎቹ ላይ ማሻሻያ በማድረግ ስጋቱን ልታመክን እንደምትችል  በመግለጽ ነው ያደማደሙት፡፡

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የሰኔ 15   ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here