በአብክመ በባሕር ዳር ከተማ ቀበሌ 15 የሚገኜው መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒየን ኃ.የተ. ሎት 1. የሰብል ሙቀት መለኪያ /Mositure Meter/ ለሁለተኛ ጊዜ፣ ሎት 2. ሚዛን ባለ መቶ የሚመዘን ለሁለተኛ ጊዜ፣ ሎት 3. የሩዝ መዝሪያ ማሽን ለሁለተኛ ጊዜ፣ ሎት 4. የጥበቃ የደንብ ልብስ ሰፌት ለሁለተኛ ጊዜ፣ ሎት 5. ዲጅታል ሚዛን ለመጅመሪያ ጊዜ፣ ሎት 6. የመኪና መለዋወጫ ግዥ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ ሎት 7. የኮምፒወተር ዕቃዎች ግዥ ለመጀመሪያ ጊዜ እና ሎት 8. የኮምፒተር ወረቀት ለመጀመሪያ ጊዜ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሽናፊው መግዛት ይፈለጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅት መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ጋራቲ /ዋስትና/ ወይም (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ ደረሰኙ ከዋጋ ማቅርቢያው ፖስታው ውስጥ በማስገባት ማያያዝ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ዋጋ የሚሆን ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) እንዳይሰበሰብባቸው ፈቃድ የተሰጣቸው (በግብር አዋጁ ከግብር ነጻ ከሆኑ) አቅርቦቶች ካልሆኑ በስተቀር በግዥው የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ዋጋ ሲሞላ እና (ሲፒኦ) ሲያሲይዙ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡ ቫት የሚጠይቀው የአንዱ ወይም በጥቅል /ሎት/ የሚገዛው እቃ እንጅ በአንድ ማስታወቂያ ለወጡ አለመሆኑ ይታወቅ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም በማድረግ እና ለጨረታው የሚያስፈልጉ ሰነዶች በፖስታው ውስጥ ማስገባትና ፖስታው ላይ ክብ ማህተም በማድረግ በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 350 (ሶስት መቶ ሃምሳ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ማስታቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ለወጣው ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ለሁለተኛ ጊዜ ለወጣው ለ7 ተከታታይ ቀናት ከዩኒየኑ ሒሳብ ክፍል ወይም ቢሮ ቁጥር 106 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ለወጣው ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 10ኛው ቀን እስከ 8፡00 ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው፡፡ በ10ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ ለወጣው ለ7 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 7ኛው ቀን እስከ 8፡00 ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው፡፡ በ7ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ቅዳሜ ዩኒየኑ የሥራ ሰዓት ሲሆን ጨረታው በሚከፈትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በዚሁ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ጨረታው ተወዳዳሪዎች /ተወካዮቻቸው/ በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተወዳዳሪዎች ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡
- የጨረታ አሽናፊው በጨረታ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ አሽናፊው የውል ማስከበሪያ ተቀባይነት ባላቸው የዋስትና ዓይነቶች የጠቅላላ የውሉን ዋጋ 10 በመቶ በማስያዝ ውል መፈጸም አለበት፡፡
- የሚፈልጉትን ሎት መርጦ መሙላት የሚቻል ሲሆን ከአንድ ሎት ውስጥ ለይቶ ወይም ቀንሶ (መርጦ) መሙላት አይቻልም፡፡ አሽናፊ የሚለየው በተናጥል ይሆናል፡፡ የሎት 4 አሽናፊ የሚለየው በጥቅል ይሆናል፡፡አሽናፊው የአሸነፈውን እቃ በፍትህ ውል ከተመረመረ (ከተመዘገብ) የምርመራም ሆነ የምዝገባ ክፍያ አሸናፊው ይከፍላል /ይሸፍናል፡፡
- አሽናፊው የአሽነፈውን እቃ በእራሱ ትራንስፖረት አጓጉዞ ሊያቀርብ ነው፡፡ ለስራተኛም ሆነ ለትራንስፖርት ማንኛውም ወጭ አሸናፊ ይሸፍናል፡፡ የሚገዙት የማንኛውም እቃዎች መጠንና (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ይገኛል፡፡
- በዚህ ያልተጠቀሱ ሀሳቦች ቢኖሩ በአብክመ ህ/ስ/ማ የግዥና ሽያጭ መመሪያ ቁጥር 58/2015 መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናሉ፡፡
- ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 09 11 59 05 34 /058 320 16 70 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒየን ኃ.የተ.

