በድጋሜ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
35

ቁጥር 21/2018

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የስልጠናና ምርምር ማዕከል ነባር ህንጻ የጥገና ሥራ ለማስጨረስ   የጠቅላላ ሥራ ተቋራጮችን ከደረጃ 7 እና በላይ የሆኑ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊዉን በመለየት ማሰራት ይፈለጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታዉ ለመወዳደር የሚፈለጉ ድርጅቶች፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ ለግንባታ ዘርፍ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት፣ ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ፎቶ ኮፒ አድርገው ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ጠቅላላ ድምር ዋጋ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁጥር 104 በመምጣት ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡ ሰነዱን በጥንቃቄ ያለምንም ሥርዝ ድልዝ በመሙላት የፋይናስ ሰነዶችን ኦርጅናል እና ኮፒ ሰነዶችን በጥንቃቄ በፖስታ ለየብቻ በማሸግ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን የጥገና  ሰነዶችን እስከ 22ኛው ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት አለባቸዉ፡፡  በጥቃቅን አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ ከአደራጃቸዉ መ/ቤት የቅርብ ጊዜ ድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ጨረታው በ22ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ይዘጋና በእለቱ ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ግዥና ንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክተር ሂደት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 103 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው በእለቱ ይከፈታል፡፡
  5. የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ የተመሰከረለት ቼክ (ስፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ይህም ሲባል በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታው የፋይናንስ ሰነድ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው የሚከፈትበት 22ኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4፡00 ይዘጋና 4፡30 ይከፈታል፡፡
  7. ኮርፖሬሽኑ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  8. የህንጻ ጥገና ሥራዉ ዓይነት፣ ብዛት እንዲሁም የውል ቃሎች ከሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ የቀረበ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  9. የጨረታ ሰነዱን አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቀበሌ 13 አየር መንገድ ከሚወስደዉ አስፓልት ገጠር መንገድ ከፍ ብሎ ባለዉ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 ድረስ በመምጣት መዉሰድ ይችላሉ፡፡
  10. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 320 97 35 /09 18 70 67 38 /09 18 70 74 85 ደውሎ መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን

ባሕር ዳር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here