በሙቀት መጨመር የሚጐዱት

0
35

የዓየር ንብረት ለውጥ ባስከተለው የሙቀት መጨመር ሳቢያ በተቦረቦረ ግንድ እና ቅርንጫፎች ውስጥ እጭ የሚፈለፍሉ የንብ መንጋዎች በመሬት ጉድጓድ ውስጥ  ከሚፈለፍሉት  የበለጠ በከፋ ደረጃ ተጐጂ መሆናቸውን ሳይንስ ዴይሊ ድረ ገጽ አስነብቧል፡፡

በአውስትራሊያ ማኳሪ ዩኒቨርሲቲ በሀገሪቱ የሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በጋራ ያደረጉትን ጥናት እና ምርምር ውጤት በመረጃ ምንጭነት እንዳሰፈረው የዓየር ንብረት ለውጥ በንቦች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል፡፡ ከነዚህ ውስጥ ደግሞ በዛፍ እና ቅርንጫፎች ላይ እጭ የሚፈለፍሉ የበለጠ ተጐጂ መሆናቸው ነው ያሰመረበት፡፡

በአውስትራሊያ አንድ ሺህ ሰባት መቶ የሚጠጉ ነባር የንብ ዝርያዎች መገኘታቸውን ያስነበበው ድረ ገጹ አብዛኛዎቹ በተቦረቦረ ግንድ ወይም ቅርንጫፍ ስንጥቃት እና ክፍተቶች ውስጥ እጭ የሚጥሉ ወይም የሚፈለፍሉ መቋቋሚያ ወይም መከለያ የላቸውም፡፡ ይህ በመሆኑም በንብ ዝርያዎቹ ርባታ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ያሳርፋል፡፡

ከንብ ዝርያዎቹ መሬት ጉድጓድ ውስጥ እንቁላል ጥለው እጭ የሚፈለፍሉት ከሌሎች በተሻለ የተጠበቁ መሆናቸውን መገንዘብ ችለዋል- ተመራማሪዎቹ፡፡

ንቦች ለስነ ምህዳር ጥበቃ ፣ለግብርና የሰብል ልማት እና ምርታመነት ሚናቸው የላቀ መሆኑን በመገንዘብ ለተጠቀሰው ችግር መፍትሄ መሻት ጠቀሜታው የጐላ መሆኑን በመግለጽ ነው ጽሁፉ የተደመደመው፡፡

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here