ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 22/2018

0
64

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን /አሚኮ/ ሎት 1 የዋናዉ ህንጻ የኢንቴሬር ዲዛይን ሥራ ከ3ኛ ፎቅ ግማሹን የማይጨምር ሁኖ ሙሉ ህንጻዉ የኢንቴሬር ዲዛይን ሥራ ሆኖ ደረጃ 3 እና በላይ በህንጻ የማማከርና የዲዛይን ፈቃድ ያላቸዉ እንዲሁም ሎት 2 ያገለገሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ ተጯራቾችን አወዳድሮ አሸናፊዉን በመለየት የኢንቴሬር ዲዛይን ማሰራት እና ያገለገሉ ዕቃዎችን መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታዉ ለመወዳደር የሚፈለጉ ድርጅቶች፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ ለግንባታ ሥራዎች የከተማ ልማት የብቃት ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ፎቶ ኮፒ አድርገው ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ጠቅላላ ድምር ዋጋ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለሎት 1 በተከታታይ ሃያ አንድ ቀናት እና ለሎት 2  አስራ አምስት ቀናት  ከቀኑ 11፡30 ድረስ  ብር 500 (አምስት መቶ ብር)   አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁጥር 106  መግዛት ይችላሉ፡፡ ለሎት 1. የቴክኒክ እና የፋይናስ ሰነዶችን ለየብቻ  በጥንቃቄ በፖስታ  በማሸግ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት ለዚህ ሲባል በተዘጋጄዉ የጨረታ ሣጥን በ22ኛዉ ቀን  ለሎት 2. የፋይናስ ሰነድ  በፖስታ በማድረግ 16ኛዉ ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት አለባቸዉ፡፡
  4. ጨረታው ለሎት 1. በ22ኛው ቀን ለሎት 2. በ16ኛዉ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ይዘጋና በእለቱ ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ግዥና ንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክተር 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው በእለቱ ይከፈታል፡፡
  5. የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ የተመሰከረለት ቼክ (ስፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህም ሲባል በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታው የፋይናንስ ሰነድ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የኢንቴሬር ዲዛይን ሥራ የቴክኒክ ዉጤቱ 70 እና በላይ ያመጡ ድርጅቶች ወደ ፋይናስ ዉድድር የሚቀርቡ ይሆናል፡፡
  6. የኢንቴሬር ዲዛይን ጨረታው የሚከፈትበት በ22ኛዉ ቀን 4፡00 ይዘጋና 4፡30 ይከፈታል፡፡ ያገለገሉ ዕቃዎች ጨረታ በ16ኛዉ ቀን 4፡00 ይዘጋና 4፡30 ይከፈታል፡፡ ቀኑ በዓል ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4፡00 ይዘጋና 4፡30 ይከፈታል፡፡
  7. ቢሮው ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  8. የሚፈለጉትን ኢንቴረር ዲዛይን፣ ያገለገሉ ዕቃዎች ዓይነት፣ ብዛትና ስፔስፊኬሽን እንዲሁም የውል ቃሎች ከሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ የቀረበ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  9. የጨረታ ሰነዱን አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቀበሌ 13 አየር መንገድ ከሚወስደዉ አስፓልት ገጠር መንገድ ከፍ ብሎ ባለዉ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 ድረስ በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
  10. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 320 97 35፣ 09 18 70 74 85፣ 09 18 70 67 38 ደውሎ መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን

ባህር ዳር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here