ያልተቋረጠው ማስጠንቀቂያ

0
25

የዓየር ንብረት  ያስከተለው የሙቀት  መጨመር በአውሮፓ ሀገራት በቀጣዮቹ ወራትም ተባብሶ የኃይል መቆራረጥ፣ የት/ቤቶች መዘጋት፣ ጐርፍ እና የባሕር ወለል ከፍታን እንደሚጨምር ተመራማሪዎች ማስጠንቀቃቸውን ኒውሳይንቲስት ድረ ገጽ ሰሞኑን አስነብቧል፡፡

ድረ ገጹ እንዳሰፈረው የሙቀት መጠኑ እየተባባሰ እንዳይሄድ ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት አቅማቸውን አሟጠው በቅንጅት ቢሰሩ ሁነቱን መቆጣጠር ይቻላል፡፡ ሆኖም እንደ እንግሊዝ ያሉ ሀገራት ዝግጁ አለመሆናቸው ነው የተጠቆመው፡፡ የተጠቀሰው ምክንያት አጥጋቢ ካልሆነ ደግሞ የዓየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የተቋቋመው ግብረ ሀይል ወይም ተቋም በተግባራዊ እንቅስቃሴው ዘግይቷል ወይም በተሳሳተ አቅጣጫ እየተጓዘ ነው የሚል ማደማደሚያ ነው ያሰፈረው -ድረ ገጹ፡፡

 

ለሙቀት መጨመሩ መባባስ የከባቢ ዓየር ብክለት ቀደም ብሎ እንደነበረው ባይሆንም አሁንም መቀጠሉን እና አማካይ ሙቀት ከሚጠበቀው በበለጠ መጨመሩ ነው የሰፈረው ፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃም ሁለት ነጥብ ስምንት ዲግሪ ሴልሺየስ ሙቀት ተጠባቂ ሆኖ ሳለ ከዚህ  የበለጠ እየጨመረ መሄዱ አስጊነቱን አመላክቷል፡፡

 

በመጨረሻም አሁንም ታዳሽ የኃይል ምንጭን በመጠቀም፣ የኤሌክትሪክ የኅይል ተሸካሚ መስመሮችን አቅማቸውን በማሻሻል ስነምህዳሮች እንዲያገግሙ በመስቻል የካርቦን ልቀትን መቀነስ ግድ መሆኑ ነው የተሰመረበት፡፡

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here