ግልጽ የጨረታ ማሰታወቂያ

0
28

የሰሜን አቸፈር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት አመት የG+4 የቢሮ ግንባታ እንዲገነባላቸው በጠየቁት መሰረት ደረጃ 3 እና ከዚያ በላይ ለጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ወይም ህንፃ ስራ ተቋራጭ ያላቸውን አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ያላቸው፡፡
  3. ተጫራቾች የሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ብር000 (ሁለት መቶ ሺ) ብር እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት)ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. የጨረታዉ ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት ግዥ ጠቅላላ ዋጋ 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ) ብር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ/1 ከሰሜን አቸ/ወ/ገ/ጽ/ቤት ዋና ገ/ያዥ በመክፈልና የከፈሉበትን ማስረጃ ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. የጨረታ ሰነዱ ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 30ኛው ቀን 11:30 ድረስ ተሽጦ በ31ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡ሆኖም ግን 31ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ መግዛት ሲመጡ የንግድ ስራ ፈቃዳቸውን የጨረታ ሰነድ ለሚሸጠው አካል ማሳየት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች ኦርጅናል እና ኮፒ የመጫረቻ ሰነዶችን ከጨረታ ማስከበሪያ ጋር በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ፤ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን በሰሜን አቸፈር ወ/ግ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 05 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. አሸናፊው ተጫራች የሚመረጠው ባቀረበው ጠቅላላ ዋጋ ስለሆነ በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የሚገኙትን የሁሉንም ዋጋ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ሙሉ በሙሉ ከጨረታው ውጭ ይደረጋሉ፤ እንዲሁም የሚሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ማስቀመጥ እና የሞሉትን ዋጋ ቫትን ጨምሮ ወይም ከቫት ውጭ መሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል ካልጻፉ ግን የተሞላው ዋጋ ቫትን እንደሚጨምር ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
  11. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል ከሰ/አቸ/ን/አስ/ቡድን ማግኘት ይችላሉ
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ይሁን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ተጫራቾች ዋጋ በሚያስቀምጡበት ጊዜ የድርጅታቸውን ማህተምና ፊርማ ሁሉን የጨረታ ሰነዶች ፖስታው ላይ በማስገባት ማሽግ ይኖርባቸዋል፤ እንዲሁም የሚሞሉት ያንዱ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ስርዝ ድልዝ በማድረግ:: የራሳቸውን ፊርማ ቢያስቀምጡም በመመሪያ ማሻሻል ምክንያት ያንዱ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ የራሳቸውን ፊርማ ቢያስቀምጡም ከውድድር ውጭ ይሆናሉ፡፡ ስለሆነም ያንዱን እና ጠቅላላ ዋጋውን ላለመሰረዝ በጥንቃቄ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ከውድድር ውጭ ይሆናሉ፡፡ በውድድሩ ወቅት 3 እና ከዚያ በላይ ከሆኑ ሲከፈት ከተነበበው አጠቃላይ ዋጋ ላይ የሂሳብ ስሌት (አርቲሜቲክ ቼክ) ከተሰራ በኋላ የተደረሰበት ልዩነት እስክ5 በመቶ ድረስ ከሆነ ተቀባይነት ሲኖረው ከዚህ የበለጠ ከሆነ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡ በውድድሩ ወቅት ከ3 እና ከዚያ በላይ ከሆኑ ሲከፈት ከተነበበው አጠቃላይ ዋጋ ላይ የሂሳብ ስሌት አርቲሜቲክ ከተሰራ በኋላ የተደረሰበት ልዩነት እስከ ሁለት ነጥብ አምስት ድረስ ከሆነ ተቀባይነት ሊኖረው፤ ከዚህ የበለጠ ከሆነ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
  14. በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር ቢሮ ቁጥር 5 በአካል በመገኘት ማግኘት ይችላሉ፤ እንዲሁም ተጫራቾች ቴክኒካልና ፋይናንሻል ዶክመንቶችን በተለያዩ ፖስታ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  15. ሌሎች በማስታወቂያው ያልተካተቱ ጉዳዩች በግዥ አፈጻጸም መመሪያው መሰረት ይስተናገዳሉ ፡፡

የሰሜን አቸፈር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here