ቫይታሚን ሲ- ለአንጐል ጤናማነት

0
5

በቫይታሚን “ሲ” የበለፀገ አመጋገብ የአንጐል ጤናን በመጠበቅ አዛውንቶች ከእድሜያቸው መጨመር ጋር ተያይዞ የማገናዘብ እና የማስታወስ ዓቅማቸው እንዳይቀንስ የማድረግ አበርክቶው የላቀ መሆኑን ሳይንስ ዴይሊ ድረ ገጽ ሰሞኑን አስነብቧል፡፡

በጃፓን ሂሮሳኪ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደ ከ64 ዓመት በላይ እድሜ ያስቆጠሩ 2000 አረጋውያንን ባካተተ ጥናት ናሙናዎችን ተንትነዋል፡፡ በቅኝታቸውም የግራጫ እና ነጭ ቁስ መጠንን ገምግመዋል፡፡

ተመራማሪዎቹ ከተሰበሰበው ናሙና ውጤት በደም ውኃ መሰል ፈሳሽ  (ኘላዝማ) ውስጥ አነስተኛ የቫይታሚን ሲመጠን የተስተዋለባቸው አነስተኛ የግራጫ ቁስ መጠን በማስታወስ እና ማገናዘብ ዓቅም ደካማ መሆናቸውን ነው ያረጋገጡት፡፡

የጥናቱ ውጤት እንዳመላከተው የቫይታሚን “ሲ” መጠንን መጠበቅ አንጐል ከእርጅና በመጠበቅ፣ የማገናዘብ ዓቅም እንዳይቀንስ መከላከል ሚናው የላቀ ነው፡፡

የተመራማሪዎቹ የቡድን መሪ ቶሙሂሮ ሺንታኩ እንዳብራሩት በደም ኘላዝማ (ነጭቁስ) ውስጥ መጠኑ ከፍ ያለ ቫይታሚን “ሲ” መገኘት በአንጐል አውታር መረብ ግንኙነቱን በማጠናከር የማገናዘብ ዓቅም እንዳይቀንስ ያደርጋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያያዞ አንጐል እንዳያረጅ ማለትም የማገናዘብ የማስታወስ ዓቅም እንዳያሽቆለቁል አበርክቶው የላቀ ነው ቫይታሚን “ሲ”፡፡

በመጨረሻም የአመጋገብን ሁኔታ ጠቀሜታውን ማወቅ እና የእለት ተእለት አመጋገብ ልምዶቻችን በአንጐላችን ላይ ያላቸውን ተፅእኖ መገንዘብ ተገቢ መሆኑን ነው ያሰመሩበት ተመራማሪዎቹ፡፡

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የሐምሌ 6 ቀን 2018 ዓ.ም  ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here