አዛውንቱ አሽከርካሪ እና ጥያቄያቸው

0
63

አሜሪካዊዉ የ93 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋ  አሽከርካሪ በረዥም ዘመን የጭነት መኪና አሽከርካሪነታቸው የዓለም የድንቃ ድንቅ መዝገብ ባለክብረ ወሰን ብሎ እንዲመዘግባቸው ጥያቄ ማቅረባቸውን ዩፒአይ ድረ ገጽ ሰሞኑን አስነብቧል፡፡

አዛውንቱ ኦሪን አስመስ በመጪው ነሐሴ   94  ዓመት ይሞላቸዋል፡፡ “ማክላውሊን ፍራይት” በተሰኘ የጭነት መኪና ማጓጓዣ ድርጅት ውስጥ በሾፌርነት ተቀጥረው በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡

የጭነት መኪና ማጓጓዣ  ድርጅቱ ፕሬዘዳንት እና ተባባሪ ባለቤት የሆኑት ዳን ማክላውሊን የኦሪን አስመሰን የሥራ ልምድ መዛግብት አገላብጠው እና ከአዛውንቱ ጠይቀው በማረጋገጥ ባለክብረ ወሰን ሊሆኑ እንደሚችሉ በማመን ለክብረ ወሰን መዝጋቢው ተቋም ጥያቄ አቅርበውላቸዋል፡፡

አሁን ላይ ዕድሜ ጠገብ የጭነት አሽከርካሪነት ክብረ ወሰን ዶይሊ አርቸር በሚባል የ92 ዓመት አዛውንት በታህሳስ 2025 እ.አ.አ  መያዙን የኦሪን አስመስ ቀጣሪ ማረጋገጣቸውንም ድረ ገጹ አስነብቧል፡፡

ኦሪን አስመስ ከ70 ዓመታት በላይ በዘለቀው የአሽከርካሪነት ዘመናቸው በአሜሪካ ከሀዋይ እና አላስካ በቀር ሁሉንም ግዛቶች ማካለላቸው ነው የተገለፀው፡፡ በዚህም ከአምስት ሚሊዬን ማይል  ወይም ስምንት ሚሊዬን ኪሎ ሜትር በላይ ማሽከርከራቸውን ነው ድረ ገጹ ያወሳው፡፡

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የሐምሌ 13  ቀን 2018 ዓ.ም  ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here