በአፈ/ በከሳሽ በአቶ አዲስ ጋሹ እና በአፈ/በተከሳሽ መምህር አየነው ነብዩ መካከል ስላለው የገንዘብ ክስ ክርክር ጉዳይ የአፈ/ተከሳሽ የተወሰነበትን ገንዘብ ለመክፍል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው በወላጅ እናቱ ወ/ሮ አለም መኮነን ስም የተመዘገበ ንብረት በቲሊሊ ከተማ ቀበሌ 01 በምሥራቅ እብስቱ ዋሴ፣ በምዕራብ መንገድ፣ በሰሜን ጌታሁን ቦረቦር እንዲሁም በደቡብ ቴሌ የሚያዋስነው የድርጅት ቤት በመነሻ ዋጋ ብር 634,644.76 (ስድስት መቶ ሰላሳ አራት ሽህ ስድስት መቶ አርባ አራት ብር ከሰባ ስድስት ሳንቲም) ሆኖ በጨረታ ይሸጣል፡፡ ስለሆነም ማስታወቂያው ከሐምሌ 13/2018 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም ድረስ ለተከታታይ 30 ቀን በጋዜጣ በማዋል ጨረታው ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 3፡30 እስከ 5፡00 ባለው ጊዜ እንዲጫረት ሲል ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
የጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ፍ/ቤት

