የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በ2019 በጀት አመት የጽሕፈት መሳሪያ ግዥ እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ በአገር አቀፍ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
| የግዥው አይነት | መለኪያ | ብዛት |
| የጽህፈት መሳሪያ | ||
| ቀይ ቢክ እስክርቢቶ 1ኛው | ፖኬት | 2 |
| ሰማያዊ ቢክ እስክረቢቶ 1ኛው | ፓኬት | 88 |
| ጥቁር ቢክ እስክርቢቶ 1ኛው | ፓኬት | 20 |
| የኮምፒውተር ወረቀት A4 | በደስታ | 500 |
| ካርቦን 3000H | በደስጣ | 5 |
| እሁ ገም | በቲዮብ | 10 |
| ትራንስፓረንሲ | በደስታ | 2 |
| ሃርድ ከቨር | በደስጣ | 5 |
| የማህተም ቀለም | በቲዮብ | 10 |
| የፕሪንተር ቀለም 26A SW | በቁጥር | 70 |
| የኮፒ ቀለምcannon IR2520/2525/2530 | በቁጥር | 10 |
| መዝገብ የውጭ 25በ35 | በቁጥር | 30 |
| ሸራ ፕላስተር | በቁጥር | 10 |
| የእስቴፕለር ሽቦ ትንሹ | በፓኮ | 8 |
| የእስቴፕለር ሽቦ ትልቁ | በፓኮ | 8 |
| ካኪ ፖስታ A4 | በደስታ | 5 |
| የእስቴፕለር መምቻ ትልቁ | በቁጥር | 10 |
| የእስቴፕለር መምቻ ትንሹ | በቁጥር | 10 |
| ማስታወሻ ደብተር ሲነር ላይን ባለ 100 ቅጠል | በቁጥር | 100 |
| ካልኩሌተር ካሲዮ | በቁጥር | 6 |
| ባለ ብረት አቃፊ ፋይል | በቁጥር | 200 |
| ኮሬክሽን ፍሉድ አኳ | በቲዮብ | 12 |
| የግዥው አይነት | መለኪያ | ብዛት |
| ኤሌክትሮኒክስ | ||
| ፍላሽ 64 ጅቢ | በቁጥር | 20 |
| የፕሪንተር ኬብል ባለ3 ሜትር | በሜትር | 12 |
| የኢንተርኔት ኬብል | በሜትር | 50 |
| ዲቫይደር | በቁጥር | 10 |
ስለዚህም የሚከተሉትን ዝቅተኛ መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃ ፎቶ ከፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ደ/ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ቢሮ 2ኛ ፎቅ የግዥና ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 22 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ስለ ዕቃው ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ኦርጅናል በአንድ ፖስታ፣ ቅጅ በአንድ ፖስታ ውስጥ እና ሰነድ በማሸግ ደ/ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ 2ኛ ፎቅ ግዥ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 22 ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ኛው ቀን 10፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለጽህፈት መሳሪያ ተወዳደሪዎች ብር 20,000 (ሃያ ሽህ) በባንክ በተመሰከረ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ ለ60 ቀናት የፀና መሆን ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 22 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የደ/ማርቆስ ከተማ አስ/ከ/መ/ል/ጽ/ቤት

