ስሜትን መግለፅ የቻለው የሮቦት የፊት ገፅ

0
57

በቻይና “ኤሄድ ፎርም” የተሰኘ ኩባንያ በሰው እና ሮቦት መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ ጥቃቅን እንቅስቃሴዎችን እና የፊት አገላለፆችን በሞተር በሚሰራ የሮቦት ጭንቅላት ሲከውን ለእይታ ማብቃቱ በርካቶችን ማስደመሙን ኦዲቲ ሴንትራል ድረ ገጽ አስነብቧል፡፡

በ2024 በኒውዮርክ በሚገኘው የኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ በፈጠራ ምህንድስና ትምህርት የተካነው ዩሀንግሁ “ብሬክዳውን ዘቤሪዬር” እንቅፋትን መሻገር በሚል በቅርቡ የሰራውን የሮቦት ምስል ለእይታ አብቅቷል፡፡

“ኤም 1” በሚል የተነደፈው የሮቦት ከአንገት በላይ ምስል የሰውን እንቅስቃሴ እና የሰሜት ለውጥ ማመላከት የቻለ ነው ተብሎለታል፡፡ይህም በማህበራዊ ሚዲያ በስፋት በመታየቱ ብዙዎችን አስደምሟል፡፡የአንገት በላይ ምስሉ በውስጡ በጥቃቅን የኤሌክትሪክ ክሮች ረቂቅ ስሜት እና እንቅስቃሴን ማሳየትም ችሏል፡፡

የሮቦት ጭንቅላቱን ለመስራት ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ግድ በማለቱ ዋጋው እስከ 150 ሺህ ዶላር እንደሚደርስ ነው ድረ ገጹ ያሰፈረው፡፡

“ኤሄድ ፎርም” ኩባንያ በቅርቡ “ኤም 1”ን ለማሻሻል እና ከከንፈር እንቅስቃሴ እና ድምፅ ጋር የተቀናጀ እምርታ ለማሳየት  መዘጋጀቱ  ነው  በማጠቃለያነት ለንባብ የበቃው፡፡

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር  የነሐሴ  4  ቀን 2018 ዓ.ም  ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here