ዳት ኢንተርናሽል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ ማህበር በምዕራብ ጎጃም ዞን በቡሬ ዙሪያ ወረዳ ቦቆ ጣቦ ቀበሌ ልዩ ቦታው ወንጅባብ ተብሎ በሚጠራው ቦታ የግራናይት ማዕድን ምርት ማምረት ሥራ ፈቃድ እንዲሰጣቸው መሥሪያ ቤታችንን ጠይቀዋል፡፡
የጂኦግራፊክ ኮኦርዲኔቶችም፡-
Adindan UTM Zone 37N
Geographic Coordinates of the license area
Block:-1
| No | Easting | Northing |
| 1 | 284631 | 1145608 |
| 2 | 284863 | 1145810 |
| 3 | 285025 | 1145761 |
| 4 | 285024 | 1145724 |
| 5 | 285120 | 1145648 |
| 6 | 285229 | 1145696 |
| 7 | 285201 | 1145405 |
| 8 | 285104 | 1145399 |
| 9 | 285007 | 1145364 |
| 10 | 284886 | 1145467 |
አዋሳኝ ቦታዎች
| በሰሜን | በደቡብ | በምዕራብ | በምሥራቅ |
| የአርሶ አደር ይዞታ መሬት | ሽጥ | ግራናይት ቦታ | የአርሶ አደር ይዞታ መሬት |
ስለዚህ የተጠየቀውን ፈቃድ ከመስጠታችን በፊት በተጠቀሰው አካባቢ በተለይም ከዚህ በላይ በተመለከቱት የጂኦግራፊክ ኮኦርዲኔቶች በሚከለል ቦታ ላይ ይገባኛል የሚል ካለ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሰባት /07/ ቀናት ውስጥ ተቃውሞውን በጽሑፍ ለመሥሪያ ቤታችን እንዲያቀርቡ እናሳስባለን፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 222 12 37/21 42 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የአብክመ ማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ

