በደቡብ ወሎ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ የሐይቅ ማረሚያ ቤት አስ/ር ጽ/ቤት የ2019 በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ ለህግ ታራሚዎች የሚያስፈለጉ ልዩልዩ ግብዓቶችን ማለትም ቀይ ጤፍ፣ ቀይ ማሽላ፣ የተዘጋጀ ጓያ ክክ፣ የተዘጋጀ ባቄላ ክክ፣ ነጭ ስንዴ፣ ነጭ በቆሎ፣ ዛላ በርበሬ፣ የምግብ ጨዉ፣ ጎመን ዘር፣ የማገዶ እንጨት፣ ሳሙናና መሰል ግብዓቶች እንደዚሁም የወጥ ቤት እቃዎችን እና የመሳሰሉትን ለምግብ አስፍላጊ ናቸዉ የተባሉትን ግብዓቶች ከመስከረም ወር ጀምሮ ለተከታታይ ስድስት ወራት ለማቅረብ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች በተቀመጠው መስፈርት መሰረት የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ ወቅታዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡
- የግዥ መጠን ብር 2,000,000 (ሁለት ሚሊዮን ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የእቃውን ወይም የአገልግሎቱን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ያስያዙበትን ደረሰኝ ኮፒ በማድረግ ከኦርጅናል የጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የዕቃውን ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሰነዱን ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መዉሰድ ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሐይቅ ማረሚያ ቤት አስ/ር ጽ/ቤት በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ነሐሴ 11/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ነሐሴ 25/2018 ዓ.ም ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ የጨረታ ገምጋሜ ኮሜቴው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ክፍል ቢሮ ቁጥር 4 በ16ኛው ቀን ነሐሴ 26/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታ መክፈት አይስተጓጉልም፡፡ ጨረታ መክፈቻው ቀን እሁድና ቅዳሜ እንዲሁም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ ሥራ ቀን በተቀመጠው ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 222 05 80 /17 በመደወል መረጃ ማገኘት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊ ተጫራች ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ5 ተከታታይ የሥራ ቀና በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ካሸነፉት እቃ ወይም አገልግሎት ጠ/ዋጋ ላይ የውል ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን 25 በመቶ (በሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ለሐይቅ ማረሚያ ቤት አስ/ር ጽ/ቤት አስይዘው ውል በመፈጸም ያሸነፉትን ዕቃ ሐይቅ ማረሚያ ቤት ንብረት ክፍል ድረስ ማስረከብ ሲኖርበታል፡፡ ውል ሳይወስዱና ንብረቱን ለማስረከብ ፈቃደኛ ሆነው ካልተገኙ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ የሚወረስ መሆኑን እንድታውቁና ንብረቱን በተሰጠው ስፔስፊኬሽን መሰረት በተሰጠዎት ጊዜ ውስጥ ማስረከብ የሚኖርብዎት ሲሆን ነቀዝ ሊበላቸዉ የሚችሉ እህሎችን በየሁለት ወሩ የሚቀርቡ ሲሆን ሊብላሹ የሚችሉ ነገሮችን መስሪያ ቤቱ ጋር በመነጋገር የሚቀርቡ መሆኑ ይታወቅ፡፡
የሐይቅ ማረሚያ ቤት አስ/ር ጽ/ቤት

