ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
31

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በዮኒሴፍ በጀት ድጋፍ ለአካል ጉዳተኛ ህፃናት የሚውል ዊልቸር ግዥ በግልጽ ጨረታ ለመግዛት የፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ካለየ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙ ዋጋ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት የችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ከግ/ፋይ/ንብ/አስ ክፍል ቢሮ ቁጠር 213 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር ወይም የዕቃው ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Gamtee) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በባህል ቱሪዚም ቢሮ በግ/ፋይ/ንብ/አስ ደጋፊ የስራ ሂደት ወይም ቢሮ ቁጥር 213 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 15ኛው ቀን ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ፋይ/ንብ/አስ ደጋፊ የስራ ሂደት ክፍል በቢሮ ቁጥር 213 በ16ኛው ቀን በ8፡00 ታሽጎ በዚያው ቀን 8፡30 ይከፈታል፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 213 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 220 42 70 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 58 64 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

አድራሻ ቀበሌ 16 ግብርና ምርምር ቢሮ ፊት ለፊት ካለው ህንጻ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 213

የአብክመ ሴቶች ወጣቶች ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ

ባሕር ዳር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here