የከተማ ቦታ ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

0
29

በደራ ወረዳ አንበሳሜ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 በፊደል ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት በ2019 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር 3 ቦታዎች ለንግድ አገልግሎት 1 ቅይጥ እና 1 መኖሪያ  በድምሩ 5 የከተማ ቦታዎችን በግልጽ የሊዝ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-

  1. መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ከ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ማዘጋጃ ቤቱ ቢሮ ቁጥር 4 በመምጣት መጫረት ይችላሉ፡፡
  2. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ከ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ብቻ ይሆናል፡፡
  3. የጨረታ ሳጥኑ የሚታሸገው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ በወጣ በ20ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 11:30 ይሆናል፡፡
  4. ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው በጋዜጣ በወጣ በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 በማዘጋጃ ቤቱ ግቢ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡ 21ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥላው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  5. ስለጨረታው ዝርዝር ማብራሪያ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ሲፒኦ) የተጫረቱበትን የቦታ ስፋት የቦታው መነሻ ዋጋ በማባዛት የሚገኘውን ውጤት ከ15 በመቶ ያላነሰ በዝግ አካውንት በማስገባት በባንክ የተመሰከረለት ሰነድ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ማዘጋጃ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 09 09 53 19 67 /09 18 55 54 23 በመደወል መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የአንበሳሜ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here