ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
40

በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የአገዉ ግምጃ ቤት ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የሶላር እና የኤሌክትሮ መካኒካል ዕቃዎች አቅርቦት ግዥ ለመግዛት ስለሚፈልግ የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት ፎቶ ኮፒ አያይዘዉ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግዥ መጠኑ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ ሰርተፊኬት ፎቶ ኮፒ አያይዘዉ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ከአገዉ ግምጃ ቤት ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በድርጅቱ ባንክ ገቢ በማድረግ ደረሰኝ በማምጣት በመ/ቤታችን መሂ-1 የሞሉትን ዋጋ 2 በመቶ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአገዉ ግምጃ ቤት ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ገቢ/ግ/ፋ/ን/አስ/ስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 02 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛዉ ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ቢገኙም ባይገኙም በአገዉ ግምጃ ቤት ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ነሐሴ 18/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 2/2018 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን በ16ኛዉ ቀን ከረፋዱ 4፡15 ታሽጎ ከረፋዱ 4፡30 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን ብሔራዊ በዓል ወይም እሁድ ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  8. ስርዝ ድልዝ ለማንበብ አስቸጋሪ የሆነ ሰነድ አሞላል ተቀባነት የለዉም፡፡
  9. ጨረታዉ ቴክኒካል ጉዳዮችን በሰነድ ላይ ያሉትን በማሟላት ማለፍ አለበት፡፡
  10. አሸናፊዉ አካል ለዉል ማስከበሪያ 10 በመቶ በባንክ የተመሰከረለት (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በድርጅቱ ባንክ ገቢ በማድረግ ደረሰኝ በማምጣት በመ/ቤታችን መሂ-1 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  11. አሸናፊ የሆነ ድርጅት ዕቃዉን እስከ አገዉ ግ/ቤት ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድረስ በራሳቸዉ ወጪ ማምጣት እና በባለሙያ በማስፈተሽ ወይም በማስመርመር ገቢ ማድረግ አለባቸዉ፡፡
  12. የተያዘ የጨረታ ማስከበሪያ አሸናፊ ድርጅቱ ዉል እንደተያዘ ለተሸናፊዎች ተመላሽ ይሆናል፡፡
  13. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  14. ስለ ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 224 04 62 በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአገው ግምጃ ቤት ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here