ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
87

በደቡብ ጎንደር ዞን የወገዳ ከተማ አስተዳደር ከ/መ/ል/ጽ/ቤት በ2019 በጀት አመት G+5 የቢሮ ህንፃ ግንባታ ሥራ እና የሬቴይኒግ ወል ግንባታ ለማሰራት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊውን መለየት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ፡- ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  • ይህ ጨረታ የሙያ (የእጅ ዋጋ ብቻ) የሚቀርብበት ነው፡፡ ዋና ዋና የግንባታ ቁሳቁስ በወገዳ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የሚቀርቡ ሲሆን ተጫራቾች የማተሪያል ዋጋ ሳይጨምር የሙያ (የእጅ) ወጋቸውን ብቻ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  • የሙያ ዋጋው የሚካተተው የሰራተኞች የሰው ሃይል ወጭ፣ የባለሙያዎች ወጭ፣ የሥራ አስተዳደር ወጭ፣ ለስራው የሚያስፈልጉ የኮንትራክተሩ የሥራ መሳሪያዎች፣ የስራ ቦታ ማደራጀትና ማስተዳደር፣ የጥራት ቁጥጥርና የስራ ደህንነት፣ የግንባታ ሥራውን በተወሰነ ጊዜ በጥራት ማጠናቀቅ በጨረታ ሰነዱ የተገለፁ ሌሎች የኮንትራክተሩ ሃላፊነቶች ነው፡፡
  • በመ/ቤቱ የሚቀርቡ ማቴሪያሎች በግንባታ ሥራው አስፈላጊ የሆኑ ዋና ዋና የግንባታ ማተሪያሎችን ያቀርባል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች የማተሪያል ዋጋ በሚያቀርቡት የሙያ ዋጋ ውስጥ መጨመር የለባቸውም፡፡

ተጫራቾች ማቅረብ ያለባቸው ሰነዶች፡-

  1. ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ (ወቅታዊ) የዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ማስረጃውን ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና በሰነዱ ላይ የተሞላው አጠቃላይ ዋጋ ብር 500,000 (አምስት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ (የቫት) ተመዝጋቢነት መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የግብር ክሪላንስ እና የቲን ምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቻውን ለእያንዳንዳዳቸው ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) የማይመለስ ገንዘብ በመክፈል የግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ዘወትር በሥራ ሰዓት ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን እና ሌሎች መረጃዎች በፖስታ በማሸግ ይህ የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ20 ተከታታይ ቀናት በወገዳ ከተማ አስተዳደር ገ/ኢ/ል/ት ጽ/ቤት የግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሰጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
  6. ጨረታው በ21 ኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው የመክፈቻ ቀኑ በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተቀመጠው ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቻው) ባይኖሩም ለመክፈት አያስተጓጉልም፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ሥራ ብር 700,000 (ሰባት መቶ ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በመ/ቤቱ ደረሰኝ በመሂ-1 በመቁረጥ ኮፒ አድርገው በጨረታ ፖስታው ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ አሸናፊነታቸው እንደተገለፀላቸው የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በመ/ቤቱ ደረሰኝ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች G+5 የቢሮ ህንፃ ግንባታ ሁለት አመት የሥራ ልምድ ማስረጃ የቴክኒክ ባለሙያዎችና የሰው ሃይል ዝርዝር ለሥራው የሚያስፍልጉ የሥራ መሳሪያዎች ማስረጃ የሥራ አፈፃፀም እቅድ የሙያ ዋጋ የሚያሳይ የዋጋ ማቅረቢያ በጨረታ ሰነዱ የሚጠየቁ ሌሎች ህጋዊ ሰነዶች የጨረታ ዋስትና (BID SECURITY) በጨረታ ሰነዱ በተገለፀው መጠን መሆን አለበት፡፡
  9. ተጫራቾች የማተሪያል ዋጋ ሳይጨምሩ የሙያ (የሥራ ዋጋ) ብቻ በBOQ ላይ መሙላት አለባቸው፡፡
  10. ተጫራቾች የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማቅረብ የሚችል፡፡
  11. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዋጋ ማንኛውም ወጭ ያጠቃለለ መሆን ይኖርበታል፡፡
  12. ተጫራቾች ከመወዳደሪያ ሃሳቡ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውንና የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
  13. የጨረታው ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ማሻሸያ ማድረግ እና በጨረታው እራሳቸው ማግለል አይችሉም፡፡ ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ እንደሚሆኑና ለወደፊቱም ከመንግስት የግዥ ጨረታ እንዳይሳተፍ የሚደረጉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ሆኖም ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች ላወጡት ዋጋ ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
  15. ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር የሚችሉ ደረጃ 4 GC ወይም ደረጃ 4 RC እና በላይ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
  16. ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉት ደረጃ 4 እና በላይ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው መሆን አለበት፡፡
  17. አንድ ተጫራች ከአንድ በላይ ሰነድ መግዛት እና ከአንድ ፕሮጀክት በላይ መወዳደር አይችልም፡፡
  18. የጨረታውን (የሥራ) ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  19. መ/ቤቱ ከጨረታ አሸናፊው የሚፈለገውን አገልግሎት ጥራቱን ሳይቀይር በመመሪያው መሰረት ሊጨምር (ሊቀንስ) ይችላል፡፡
  20. በጨረታው የተጋነነ ዝቅተኛ ዋጋ ሞልተው አሸናፊ ሆነው የሚመረጡ የግንባታ ተቋራጮች ውል ይዘው ወደ ሥራ ሲገቡ የቅድሚያ ክፍያ አይፈቀድላቸውም፡፡ እንዲሁም በአ/ብ/ክ/መ የግዥ መመሪያ ቁጥር 144/2018 አዋጅ ቁጥር 306/2018 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
  21. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 667 04 03 /058 667 03 89 እንዲሁም በአካል በመቅረብ  መረዳት ይችላሉ፡፡

የወገዳ ከተማ አስተዳደር ገ/ኢ/ል/ት/ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here