ፕራይም ኬር የህክምናና የጤና ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሐኪም አባላቱ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ባለመቻላቸውና መጉላላት፣ ንትርክና ጭቅጭቅ በመፍጠራቸው በድርጅቱና ማህበርተኞች ላይ ኪሳራና ጉዳት እየቀጠለ በመምጣቱ ምክንያት ማህበሩ እንዲፈርስ ተወስኗል፡፡ ስለሆነም በንግድ ህግ አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 474/1 መሰረት የማህበሩ ገንዘብ ብር 2,180,000 (ሁለት ሚሊዮን አንድ መቶ ሰማኒያ ሽህ ብር) ሲሆን የማህበሩ አባልና ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ መንገሻ አበበ እና የማህበሩ አባልና ገንዘበብ ያዥ የሆኑት አቶ ደሳለኝ መኩሪያው በንግድ ህ አንቀጽ 475 መሰረት የተሾሙ ሂሳብ አጣሪዎች ሲሆኑ ስልጣናቸውም የድርጅቱን ሂሳብ የማጣራት፣ ሃብትና ዕዳ መግለጫ ማዘጋጀት፣ የማህበርተኞችን ድርሻ ለይቶ ማስቀመጥ እና ድርጅቱን ከአባላት መካከል ተረክቦ የሚያስቀጥለው አባል ካለ ከሂሳብ ማጣራት በኋላ ተደራድሮ የማስረከብና ዝውውሩን የማስፈፀም ወይም ንብረቱን በጨረታ ወይም በድርድር ተሸጦ ለዕዳና ከአባላት ክፍፍል እንዲውል የተሻለውን መርጦ ማስተግበር እና ሌሎች በንግድ ህጉ የተመለከቱት ስልጣንና ኃላፊነት ተሰጧቸዋል፡፡ በዚህም መሰረት በማህበሩ ላይ ዕዳ አለኝ ወይም ገንዘብ ጠያቂ ነኝ የምትሉ አካላት ማስረጃችሁን በመያዝ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለሂሳብ አጣሪዎች ሪፖርት እንድታደርጉ ጥሪ እናቀርባለን፡፡
አድራሻ፡- የሂሳብ አጣሪዎችን ደብረ ማርቆስ ስታር ቢዝነስ ሴንተር 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 219 ማግኘት ይችላሉ፡፡
ፕራይምኬር የህክምናና የጤና ደህንነት ኃ/የተ/የግ/ማህበር

