የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ገንዘብ ዋና መምሪያ የጓንጓ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ለ2019 በጀት ዓመት የእንስሳት መድሃኒት እና ቁሳቁስ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ጋር ውል በመያዝ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ማለትም የንግድ ፈቃድ፣ ቲን ሰርተፊኬት የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ውስጥ በማስገባት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ በጋዜጣ ከወጣበት ከነሐሴ 18/2018 እስከ ጳጉሜ 4/2018 ዓ.ም 11፡30 ድረስ የጨረታ ሰነዱ ጓንጓ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጠር 5 የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) መግዛት ይችላሉ፡፡
- የማወዳደሪያ ስርዓቱ የጨረታ አሸናፊ የሚለየው በጥቅል ነው፡፡
- የሁሉም የዕቃ አይነቶች ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ድምር ብር 30,000 (ሰላሳ ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በመ/ቤታችን የገቢ ደረሰኝ መሂ-1 ገቢ በማድረግ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ ጓንጓ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግ/ን/አስ/ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት እለት ነሐሴ 18/2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት እስከ ጳጉሜ 4/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ድረስ የጨረታ ሳጥኑ ከመታሸጉ በፊት የመጫረቻ ሰነዱን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቻው በተገኙበት በጓንጓ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በ16ኛው ቀን የጨረታ ሳጥኑ ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ 4፡15 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 16ኛው ቀን ወይም የሚከፈትበት ቀን ብሔራዊ በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ 4፡15 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቻው ካልተገኙ የጨረታ ሰነዱ እንዲከፈት ተደርጎ ያልተገኙ ተጫራቾች ግን በዕለቱ ለሚተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዕቃ በጓንጓ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በራሳቸው ወጭ በማምጣት በባለሙያና በጥራት አረጋጋጭ ኮሚቴዎች በማስፈተሽ ወይም በማስመርመር የማስረከብ ግዴታ አለባቸው፡፡ የሚሞላው ዋጋ ማንኛውም የመንግስት ታክስን ያካተተ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ተንተርሶ መጫረት የተከለከለ ነው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበው የንግድ ፈቃድ እና ቲን እንዲሁም የሚሞላቸው ሰነዶች ለሦስተኛ ወገን በግልጽ የሚታይና ሥርዝ ድልዝ የሌለበት መሆን አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የግዥውን መጠን 20 በመቶ የመጨመር የመቀነስ መብት አለው፡፡
- ተጫራቾች በግዥ መመሪያ ተገዥ መሆን አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 225 50 50 /058 225 00 09 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የጓንጓ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

