በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ ቢሮ በአዋጅ ቁጥር 280/2014 አንቀጽ 24 ንዑስ አንቀጽ 10 በተሰጠው ስልጣን መሠረት በክልል ቢሮዎች፣ በከተማ አስተዳደሮች፣ በዞኖችና በወረዳዎች የሚገኙ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ማለትም፡- (መኪናዎች እና ባለ 3 እግር ባጃጅ) ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡-
- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት በጨረታው የመሳተፍ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የተሽከርካሪዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ በጨረታ ሠነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ከግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 101 በመክፈል ከነሐሴ 20/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ መስከረም 05/2019 ዓ/ም 4፡00 ድረስ የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳደሩበትን ተሽከርካሪ የሞሉትን የጠቅላላ ድምር ዋጋዉን 10 በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም 60 ቀን ያላነሰ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በአንድ የባንክ ዋስትና ወይም (ሲፒኦ) በአብክመ ገንዘብ ቢሮ ስም በማሰራት በአንድ ፖስታ ብቻ በማሸግ በተዘጋጀዉ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የተሽከርካሪ ዋጋ የሞላበትን ገጽ ብቻ ዋናውን /original/ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 502 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ከነሐሴ 20/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ መስከረም 05/2019 ዓ/ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለሽያጭ የቀረቡ ተሽከርካሪዎችን በተዘጋጀዉ የዋጋ ማቅረቢያ ሠንጠረዥ ላይ በተገለፀዉ ቦታ ከነሐሴ 20/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ መስከረም 05/2019 ዓ/ም 4፡00 ድረስ ተሽከርካሪዎች ባሉበት ቦታ በመሄድ በአካል ማየት ይችላሉ፡፡ ርክክብ የሚፈጸመዉም በጨረታ ሠነዱ ላይ በተቀመጠዉ ቦታ ነዉ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 502 መስከረም 05/2019 ዓ/ም 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን መስከረም 05/2019 ዓ/ም 4፡30 ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚሆነዉ በተናጠል በተሰጣቸው የሠሌዳ ቁጥር ወይም መለያ ቁጥር መሰረት ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በፖስታቸዉ ላይ ስም ከነአያት፣ ፊርማና ስልክ ቁጥር መፃፍና እንዲሁም መታወቂያ ደብተር ፎቶ ኮፒ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
- ቢሮዉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 220 45 07 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- አድራሻ፡- ባሕር ዳር ከተማ ከድሮዉ ዲፖ አካባቢ ይገኛል፡፡
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ ቢሮ

