ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
42

የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የቻግኒ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የገቢ ግዥ ፋይ/ን/አስ/የስራ ሂደት በያዘው በ2019 በጀት አመት የፋይናንስና የንብረት እንቅስቃሴ ስራ ኦዲት አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ ኦዲት ማስደረግ እና ሶላርና የኤሌክትሮ መካኒካል እቃዎች አቅርቦት ግዥ ለመግዛት ስለሚፈልግ የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ፎቶ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት ፎቶ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግዥ መጠኑ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ ሰርተፊኬት ፎቶ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል የቻግኒ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገ/ት ድርጅት ቢሮ ቁጥር-4 ሰነዱን በመግዛት መጫረት ይችላሉ፡፡
  5. የማወዳደሪያ ስርዓቱ በጥቅል ነው፡፡
  6. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በመ/ቤታችን መሂ-1 የሞሉትን ዋጋ 2 በመቶ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቻግኒ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገ/ት ድርጅት የገቢ ግዥ ፋይ/ን/አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር-4 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛዉ ቀናት እስከ 4፡15 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ቻግኒ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡16 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን ብሄራዊ በዓል ወይም እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  9. የኦዲት አገልግሎት ጨረታ በቴክኒካል ዉጤት 70 በመቶ እና በላይ ያገኙ ተጫራቾች ብቻ ለዋጋ ዉድድር እንዲገኙ ጥሪ ይደረግላቸዋል፡፡ በቴክኒክ መስፈርቱ ከ70 በመቶ በታች ያገኙ ተወዳዳሪዎች የዋጋ ማወዳደሪያ ሰነድ ሳይከፈት ይመለስላቸዋል፡፡
  10. ሥርዝ ድልዝ ያለው የዋጋ አሞላል ተቀባይነት የለውም፡፡
  11. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የማሻሻያ ጥያቄ ለግዥ ፈጻሚ አካል ማቅረብ የሚችሉት ለጨረታ መወዳደሪያ ሃሣብ ማቅረቢያ ከተወሰነ ጊዜ ገደብ ከ5 ቀን በፊት ማቅረብ ይችላሉ፡፡
  12. አሸናፊዉ አካል ለውል ማስከበሪያ 10 በመቶ (በሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በመ/ቤታችን መሂ-1 ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  13. አሸናፊ የሆነው ድርጅት በራሳቸው ወጪ እስከ ቻግኒ ከተማ ዉሃና ፍሳሽ አገ/ት ድርጅት ድረስ በማምጣትና በባለሙያ በማስፈተሽ ወይም በማስመርመር የማስረከብ ግዴታ አለበት፡፡ ኦዲት የሚመረመረውም ቻግኒ ድረስ በመምጣት ነው፡፡
  14. የተያዘው የጨረታ ማስከበሪያ አሸናፊ ድርጅቱ ውል እንደተያዘ ለተሸናፊዎች ተመላሽ ይሆናል፡፡
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቻግኒ ከተማ ውሃና ፋሳሽ አገ/ት ድርጅት የገቢ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 058 225 09 04 /02 22/00 33 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የቻግኒ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here