በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የቻግኒ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሎት 1. መድሀኒት አመታዊ ውል በመያዝ ለመግዛት እና ሎት 2. ባዞላ ንጣፍ ለአንድ ጊዜ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉ፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- መድሀኒት እና ባዞላ ንጣፍ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ሰነዱን ቻግኒ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የዕለት ገቢ ሰብሳቢ ቢሮ ቁጥር 5 የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ሰነዱ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት መድሀኒት እና ባዞላ ንጣፍ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ከሆስፒታሉ ገቢ ደረሰኝ በመቁረጥ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ ማስያዝ አለባቸው፡፡ ነገር ግን የጨረታ ማስከበሪያ በቼክ ካስያዙ ከውድድር ውጭ ይሆናሉ፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሰነዱን በመሙላት ከሌሎች ማስረጃዎች ጋር በአንድ ኦርጅናል ፖስታ በማሸግ ለ22 ተከታታይ ቀናት በመሙላት እስከ 11፡30 ለግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 47 ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ቻግኒ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 47 በ23ኛው ቀን ታሽጎ በዚያው ቀን ከረፋዱ 3፡30 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሸጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የገዙትን የጨረታ ሰነድ በእያንዳንዱ ገፅ በመፈረም የድርጅቱን ማህተም በማድረግ መመለስ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ያሸነፉበትን መድሀኒት እና ባዞላ ንጣፍ በተሰጠዉ የጊዜ ገደብ የማስረከብ ግዴታ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቁ ነው፡፡
- ውድድሩ በለቀማ መሆኑን አውቀው የተጠየቁትን ሙሉ በሙሉ እንዲሞሉልን እንጠይቃለን፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 556 20 09 ወይም ቻግኒ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ገ/ፋ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 47 ድረስ በአካል በመገኘት መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ቻግኒ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

