ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
11

የውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የአካባቢ ግልጽ ጨረታ መመሪያ 17/2018 መሰረት የውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የጫኝና አውራጅ አገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ከሆኑ ድርጅቶች ለመግዛት ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉን ተወዳዳሪዎች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መሰረት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፡-

  1. የዘመኑን ግብር ከፍለው በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸዉ፤ የቫት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች በኮርፖሬሽኑ ስም የተሰራ ሲፒኦ ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ የሚከፈል (Unconditional Bid bond guarantee) ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር) ማስያዝ አለባቸው:: አሸናፊው ከተለየና ውል ከተፈረመ በኋላ ላሸነፉ ድርጅቶች የጨረታ ማስከበሪያ ይመለስላቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 ተከታታይ ቀናት በማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር ) መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በዋጋ መሙያ ሰንጠረዡ በተገለፀው መጫንና ማውረድ የአገልግሎት ግዥ የሚሰሩበትን ማስረጃዎችና የሚሞሉትን ዋጋ ኦርጅናል እና ኮፒ ማቅረብ አለባቸው::
  5. ለዋና ቢሮ ፕላስቲክ ፋብሪካ ለሚገኘው ቢሮ እና ማሰልጠኛ ማዕከል እንዲሁም ባሕር ዳር ከተማ ላይ ለሚገዙ ማንኛውም የተለያዩ ዕቃዎችን የመጫንና የማውረድ ሥራ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች የምናወዳድር ይሆናል፡፡
  6. በጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ማድረግ አይቻልም፤ ካለ ግን ዋጋውን የሞላው አካል መፈረም ይኖርበታል፡፡ በሚቀርቡ የጨረታ ሰነዶች ላይ ህጋዊ የድርጅቱ ተወካይ ስም፣ ፊርማ እና ማህተም ያረፈበት መሆን ይኖርበታል፡፡
  7. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ባሕር ዳር ከተማ ከሚገኘው ዋና መ/ቤታችን ውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁጥር 25 በመቅረብ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
  8. የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20ኛው ቀን 8:00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8:30 ይከፈታል:: የመክፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ አይችሉም፡፡
  9. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ይህንም በሚያደርግበት ጊዜ በኮርፖሬሽኑ የማስታወቂያ መለጠፊያ ቦርድ ማስታወቂያው ይገለፃል፡፡

ማሳሰቢያ፡- ለበለጠ መረጃ፡- 058-222-1479 /093011746 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የውኃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here